የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የቱ እንደሚያፈራ አታውቁም!
    መጠበቂያ ግንብ—2008 | ሐምሌ 15
    • የእርሾው ምሳሌ

      9, 10. (ሀ) ኢየሱስ ስለ እርሾው በተናገረው ምሳሌ ላይ ያጎላው ነጥብ ምንድን ነው? (ለ) በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እርሾ አብዛኛውን ጊዜ ምንን ለማመልከት ተሠርቶበታል? ኢየሱስ እርሾን ከመጥቀሱ ጋር በተያያዘ የትኛውን ጥያቄ እንመረምራለን?

      9 እድገት በሰብዓዊ ዓይን ሁልጊዜ ላይታይ ይችላል። ኢየሱስ ቀጥሎ በሰጠው ምሳሌ ላይ ይህንን ነጥብ የሚያጎላ ሐሳብ ሲናገር እንዲህ ብሏል:- “መንግሥተ ሰማይ ሴት ወስዳ ሊጡ በሙሉ እስኪቦካ ድረስ በሦስት መስፈሪያ ዱቄት ውስጥ በመደባለቅ የሸሸገችውን እርሾ ትመስላለች።” (ማቴ. 13:33) እዚህ ላይ የተጠቀሰው እርሾ ምን ያመለክታል? እርሾው የአምላክ መንግሥት ከሚያደርገው እድገት ጋር የሚዛመደውስ እንዴት ነው?

      10 በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እርሾ አብዛኛውን ጊዜ ኃጢአትን ለማመልከት ተሠርቶበታል። ሐዋርያው ጳውሎስ፣ በጥንቷ የቆሮንቶስ ጉባኤ የነበረ አንድ ኃጢአተኛ ስላሳደረው መጥፎ ተጽዕኖ ሲገልጽ እርሾን በዚህ መንገድ ተጠቅሞበታል። (1 ቆሮ. 5:6-8) ታዲያ ኢየሱስ ከላይ ባለው ጥቅስ ላይ እርሾን የጠቀሰው መጥፎ የሆነ ነገር እድገት ስለማድረጉ ለመናገር ነበር?

      11. እርሾ በጥንቷ እስራኤል ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውለው እንዴት ነበር?

      11 ለዚህ ጥያቄ መልስ ከማግኘታችን በፊት ሦስት መሠረታዊ ነጥቦችን ልብ ማለት ያስፈልገናል። አንደኛ፣ ይሖዋ የፋሲካ በዓል ሲከበር ሕዝቡ በእርሾ እንዳይጠቀም የከለከለ ቢሆንም በሌሎች ጊዜያት እርሾ የተጨመረባቸው መሥዋዕቶችን ተቀብሏል። እርሾ፣ ለምስጋና ከሚቀርበው የኅብረት መሥዋዕት ጋር በተያያዘ ጥቅም ላይ ይውል ነበር፤ መሥዋዕቱን የሚያቀርበው ሰው ይሖዋ ለሰጠው በረከቶች አመስጋኝ መሆኑን በሚያሳይ መንፈስ ስጦታውን በፈቃደኝነት ያቀርባል። ይህም በማዕዱ ለሚካፈሉ ሁሉ ደስታ ያስገኝላቸው ነበር።—ዘሌ. 7:11-15

      12. መጽሐፍ ቅዱስ በምሳሌያዊ አነጋገር ስለሚጠቀምበት መንገድ ምን ግንዛቤ አግኝተናል?

      12 ሁለተኛ፣ በቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ አንድ ነገር አንዳንድ ጊዜ በአሉታዊ መንገድ ቢሠራበትም በሌላ ጊዜ ደግሞ ያው ነገር በጥሩ ጎኑ ሊሠራበት ይችላል። ለምሳሌ ያህል፣ በ1 ጴጥሮስ 5:8 ላይ ሰይጣን፣ አደገኛና ጨካኝ መሆኑን ለማመልከት በአንበሳ ተመስሏል። ራእይ 5:5 ደግሞ ኢየሱስን ከአንበሳ ጋር በማመሳሰል “ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ” ይለዋል። ከኢየሱስ ጋር በተያያዘ አንበሳ፣ ድፍረት የተሞላበት ፍትሕን ያመለክታል።

      13. ኢየሱስ ስለ እርሾ የተናገረው ምሳሌ ከመንፈሳዊ እድገት ጋር በተያያዘ ምን ያመለክታል?

      13 ሦስተኛ፣ ኢየሱስ በምሳሌው ላይ እርሾው ሊጡን በሙሉ እንዳበላሸውና ከጥቅም ውጭ እንዳደረገው አልተናገረም። እዚህ ላይ ኢየሱስ የተለመደውን የዳቦ አዘገጃጀት መግለጹ ነበር። ሴትየዋ እርሾውን ከዱቄቱ ጋር የቀላቀለችው ሆን ብላ ሲሆን ጥሩ ውጤትም አስገኝቶላታል። እርሾው በዱቄቱ ውስጥ ተሸሽጎ ነበር። በመሆኑም እርሾው፣ ሊጡ እንዲቦካ የሚያደርግበት መንገድ ከሴትየዋ እይታ የተሰወረ ነበር። ይህ ምሳሌ፣ ዘር ዘርቶ ሌሊት የሚተኛውን ሰው ያስታውሰናል። ኢየሱስ “[ሰውየው] ሳያውቅ ያ ዘር በቅሎ ያድጋል” በማለት ተናግሯል። (ማር. 4:27) አንድ ሰው መንፈሳዊ እድገት የሚያደርግበትን መንገድ ማየት እንደማይቻል የሚገልጽ እንዴት ያለ ቀላል ምሳሌ ነው! መጀመሪያ ላይ ግለሰቡ የሚያደርገውን እድገት መመልከት አንችል ይሆናል፤ ውሎ አድሮ ግን ውጤቱ በግልጽ ይታያል።

      14. እርሾው ሊጡን በሙሉ እንዲቦካ ማድረጉ ከስብከቱ ሥራ ጋር በተያያዘ ምን ያመለክታል?

      14 ይህ እድገት የሚካሄድበት መንገድ በሰብዓዊ ዓይን የማይታይ ከመሆኑም ባሻገር እድገቱ የሚከናወነው በመላው ምድር ላይ ነው። ይህም ስለ እርሾው በሚናገረው ምሳሌ ላይ የተጠቀሰው ሌላው ነጥብ ነው። እርሾው ‘ሦስት መስፈሪያ ዱቄት’ የሚሆነው ሊጥ በሙሉ እንዲቦካ አድርጓል። (ሉቃስ 13:21 የ1954 ትርጉም) የደቀ መዛሙርት ቁጥር እንዲጨምር ያደረገው የመንግሥቱ ስብከት ሥራ፣ ልክ እንደ እርሾ በጣም ስለተስፋፋ በአሁኑ ጊዜ ስለ አምላክ መንግሥት “እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ” እየተሰበከ ነው። (ሥራ 1:8፤ ማቴ. 24:14) ስለ አምላክ መንግሥት በመስበኩ ሥራ ለተገኘው ለዚህ አስደናቂ እድገት አስተዋጽኦ ማድረጋችን እንዴት ያለ ታላቅ መብት ነው!

  • የቱ እንደሚያፈራ አታውቁም!
    መጠበቂያ ግንብ—2008 | ሐምሌ 15
    • 20, 21. (ሀ) ኢየሱስ እድገት ማድረግን በተመለከተ የተናገራቸውን ምሳሌዎች በመመርመራችን ምን ትምህርት አግኝተናል? (ለ) አንተስ ምን ለማድረግ ቆርጠሃል?

      20 ኢየሱስ እድገት ማድረግን በተመለከተ የተናገራቸውን ምሳሌዎች በአጭሩ በመመርመራችን ምን ትምህርት አግኝተናል? አንደኛ፣ የሰናፍጩ ዘር ካደረገው እድገት ጋር በሚመሳሰል መልኩ ለአምላክ መንግሥት ምሥራች ምላሽ የሚሰጡ ሰዎች ቁጥርም በከፍተኛ ሁኔታ አድጓል። የይሖዋ ሥራ እንዳይከናወን ሊያግደው የሚችል ምንም ነገር የለም! (ኢሳ. 54:17) ከዚህም በተጨማሪ በዛፉ ‘ጥላ ሥር ለመስፈር’ የፈለጉ ሁሉ መንፈሳዊ ጥበቃ አግኝተዋል። ሁለተኛው ትምህርት ደግሞ የሚያሳድገው አምላክ መሆኑ ነው። ዱቄት ውስጥ የተሸሸገው እርሾ ሊጡን በሙሉ እንዲቦካ እንዳደረገው ሁሉ ከመንግሥቱ ሥራ ጋር በተያያዘ የተከናወነውን እድገትም ሁልጊዜ ማስተዋል ወይም መረዳት ባንችልም እድገቱ ግን እየተካሄደ ነው! ሦስተኛ፣ ለመንግሥቱ ምሥራች ምላሽ የሰጡ ሰዎች ሁሉ ጥሩ ዓሣዎች ናቸው ማለት አይደለም። አንዳንዶች በኢየሱስ ምሳሌ ላይ እንደተጠቀሱት መጥፎ ዓሣዎች ሆነዋል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ