-
‘እርስ በርሳችሁ ፍቅር ይኑራችሁ’መጠበቂያ ግንብ—2003 | የካቲት 1
-
-
5, 6. (ሀ) ኢየሱስ ምን ሁለት አጫጭር ምሳሌዎች ተናገረ? (ለ) እነዚህ ምሳሌዎች ስለ ይሖዋ ምን ያስተምሩናል?
5 ይሖዋ ጠፍተው ስለባዘኑት አገልጋዮቹ ያለውን አመለካከት ለማስተማር ኢየሱስ ለአድማጮቹ ሁለት አጫጭር ምሳሌዎችን ነገራቸው። አንደኛው ስለ እረኛ የሚናገር ሲሆን እንዲህ ይላል:- “መቶ በግ ያለው ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋ፣ ዘጠና ዘጠኙን በበረሃ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘው ድረስ ሊፈልገው የማይሄድ ከእናንተ ማን ነው? ባገኘውም ጊዜ ደስ ብሎት በጫንቃው ይሸከመዋል፤ ወደ ቤትም በመጣ ጊዜ ወዳጆቹንና ጐረቤቶቹን በአንድነት ጠርቶ:- የጠፋውን በጌን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ ይላቸዋል። እላችኋለሁ፣ እንዲሁ ንስሐ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል።”—ሉቃስ 15:4-7
-
-
‘እርስ በርሳችሁ ፍቅር ይኑራችሁ’መጠበቂያ ግንብ—2003 | የካቲት 1
-
-
ይጥፉ እንጂ ውድ ናቸው
8. (ሀ) እረኛውና ሴቲቱ የጠፋባቸው ንብረት እንዳለ ሲያውቁ ምን አደረጉ? (ለ) የጠፋባቸውን ፈልገው ለማግኘት የወሰዱት እርምጃ ለንብረቱ ያላቸውን አመለካከት የሚገልጽልን እንዴት ነው?
8 በሁለቱም ምሳሌዎች ውስጥ አንድ ነገር እንደጠፋ ተገልጿል፤ ሆኖም ባለቤቶቹ ምን እንዳደረጉ ልብ በል። እረኛው ‘99ኙ እስካሉልኝ ድረስ ለአንዱ ምን አስጨነቀኝ? አንዱ ቢጠፋ ምንም አያጎድለኝም’ አላለም። ሴትየዋም ‘ለአንዲት ድሪም ምን አስጨነቀኝ? ዘጠኝ ድሪም ካለኝ ይበቃኛል’ አላለችም። ከዚህ ይልቅ እረኛው አንድ በግ ብቻ ያለው ይመስል የጠፋውን ለማግኘት ፍለጋውን ተያያዘው። ሴትየዋም ከዚያ ሌላ ድሪም የሌላት ይመስል መጥፋቱ በጣም ቆጭቷታል። በሁለቱም ምሳሌዎች ውስጥ ባለቤቶቹ ውድ የሆነ ነገር እንደጠፋባቸው ተሰምቷቸዋል። ይህ ምን ያስተምረናል?
9. እረኛውና ሴትየዋ ለጠፋባቸው ንብረት የሰጡት ትኩረት የምን ምሳሌ ነው?
9 ኢየሱስ እያንዳንዱን ምሳሌ ተናግሮ ካበቃ በኋላ “እንዲሁ . . . ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል” እና ‘እንዲሁ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ደስታ ይሆናል’ እንዳለ ልብ በል። እረኛውና ሴትየዋ ለጠፋባቸው ንብረት የሰጡት ትኩረት ይሖዋና ሰማያዊ ፍጥረታቱ ምን እንደሚሰማቸው በመጠኑም ቢሆን ያሳያል። የጠፋው ነገር ለእረኛውም ሆነ ለሴትየዋ ውድ እንደሆነ ሁሉ ባዝነው ከሕዝቦቹ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ያቋረጡ ሰዎችም በይሖዋ ፊት ውድ ናቸው። (ኤርምያስ 31:3) እንደዚህ ያሉ ግለሰቦች በመንፈሳዊ ተዳክመው ይሆናል፤ ዓመፀኞች ናቸው ማለት ግን አይደለም። በመንፈሳዊ ይድከሙ እንጂ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ይሖዋ ያወጣቸውን መስፈርቶች ይጠብቁ ይሆናል። (መዝሙር 119: 176፤ ሥራ 15:28, 29) በመሆኑም ይሖዋ ከዚህ በፊትም እንዳደረገው ሁሉ ወዲያውኑ “ከፊቱ አልጣላቸውም።”—2 ነገሥት 13:23
10, 11. (ሀ) ከጉባኤ የጠፉ ሰዎችን እንዴት ልንመለከታቸው ይገባል? (ለ) ኢየሱስ በተናገራቸው ሁለት ምሳሌዎች መሠረት አሳቢነታችንን ልንገልጽላቸው የምንችለው እንዴት ነው?
10 እንደ ይሖዋና እንደ ኢየሱስ ሁሉ እኛም በመንፈሳዊ ለደከሙትና ከክርስቲያን ጉባኤ ለጠፉት ሰዎች ከልብ እናስባለን። (ሕዝቅኤል 34:16፤ ሉቃስ 19:10) በመንፈሳዊ የደከመን ሰው እንደጠፋ በግ እንጂ የመመለስ ተስፋ እንደሌለው አድርገን ማየት አይኖርብንም። ‘ስለ ደከመ ሰው ምን አሳሰበኝ? የእርሱ መኖር አለመኖር በጉባኤው ላይ የሚያመጣው ለውጥ የለም’ ብለን ማሰብ አይኖርብንም። ከዚህ ይልቅ የጠፉትን ሆኖም መመለስ የሚፈልጉትን ሰዎች ይሖዋ እነርሱን በሚያይበት መንገድ ይኸውም ውድ እንደሆኑ አድርገን እንመለከታቸዋለን።
-
-
‘እርስ በርሳችሁ ፍቅር ይኑራችሁ’መጠበቂያ ግንብ—2003 | የካቲት 1
-
-
ቅድሚያውን ውሰዱ
12. ‘የጠፋውን ለመፈለግ እንደሚሄድ’ የሚጠቁመው ሐሳብ ስለ እረኛው ምን ይገልጽልናል?
12 ኢየሱስ ከሁለቱ ምሳሌዎች ውስጥ በመጀመሪያው ላይ እረኛው ‘የጠፋውን ለመፈለግ እንደሚሄድ’ ተናግሯል። እረኛው ቀዳሚ በመሆን የጠፋውን በግ ፈልጎ ለማግኘት ጥረት አድርጓል። አስቸጋሪና አደገኛ ሁኔታ እንዲሁም ርቀት አላገደውም። እንዲያውም እረኛው “እስኪያገኘው ድረስ” ፍለጋውን ቀጥሏል።—ሉቃስ 15:4
13. በጥንት ዘመን የኖሩ የታመኑ የአምላክ አገልጋዮች ማበረታቻ የሚያስፈልጋቸውን የረዱት እንዴት ነበር? እነዚህን የመጽሐፍ ቅዱስ ምሳሌዎች መኮረጅ የምንችለውስ እንዴት ነው?
13 በተመሳሳይም፣ ማበረታቻ የሚያስፈልገውን ሰው ለመርዳት በመንፈሳዊ ብርቱ የሆነው ሰው ቀዳሚ መሆን ይኖርበታል። በጥንት ዘመን የኖሩ የታመኑ ሰዎች ይህን ሁኔታ በደንብ ተረድተው ነበር። ለምሳሌ ያህል የንጉሥ ሳኦል ልጅ ዮናታን የልብ ጓደኛው ዳዊት ማበረታቻ እንደሚያስፈልገው በተገነዘበ ጊዜ ‘ተነሥቶ ዳዊት ወደሚገኝበት ወደ ጥሻው ሄዶ በእግዚአብሔር ስም አበርትቶታል።’ (1 ሳሙኤል 23:15, 16) ከብዙ መቶ ዓመታት በኋላም አገረ ገዥው ነህምያ ከአገሩ ልጆች መካከል አንዳንዶቹ ተስፋ እንደቆረጡ ባየ ጊዜ ‘ተነስቶ’ “የተፈራውን ጌታ አስቡ” በማለት አበረታታቸው። (ነህምያ 4:14) በዛሬው ጊዜ እኛም በመንፈሳዊ የደከሙትን ለማበረታታት ቀዳሚ ሆነን ‘መነሳት’ ይኖርብናል። ይሁን እንጂ ከጉባኤ አባላት መካከል እንዲህ ማድረግ የሚኖርባቸው እነማን ናቸው?
14. በክርስቲያን ጉባኤ ውስጥ በመንፈሳዊ የደከሙትን ወንድሞች መርዳት የሚኖርባቸው እነማን ናቸው?
14 በተለይ ደግሞ ክርስቲያን ሽማግሌዎች ‘የደከሙትን እጆች የማበርታት፣ የላሉትን ጉልበቶች የማጽናት እንዲሁም ፈሪ ልብ ያላቸውን በርቱ አትፍሩ የማለት’ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል። (ኢሳይያስ 35:3, 4፤ 1 ጴጥሮስ 5:1, 2) ይሁን እንጂ ጳውሎስ ‘የተጨነቁ ነፍሳትን አጽናኗቸው’ እና ‘ደካሞችን ደግፏቸው’ በማለት የሰጠው ማበረታቻ ሽማግሌዎችን ብቻ የሚመለከት እንዳልሆነ ልብ ማለት ይገባል። ከዚህ ይልቅ ጳውሎስ ደብዳቤውን የጻፈው “ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች ቤተ ክርስቲያን” ነበር። (1 ተሰሎንቄ 1:1፤ 5:14 NW ) በመንፈሳዊ የደከሙ ወንድሞችን መርዳት ለሁሉም ክርስቲያኖች የተሰጠ ኃላፊነት ነው። በምሳሌው ውስጥ እንደተጠቀሰው እረኛ እያንዳንዱ ክርስቲያን ‘የጠፋውን ፍለጋ ለመሄድ’ መነሳት ይኖርበታል። እርግጥ ነው እንዲህ ያለው ጥረት ይበልጥ ውጤታማ የሚሆነው ከሽማግሌዎች ጋር ተባብረን ስንሠራ ነው። አንተስ በጉባኤህ የሚገኝ በመንፈሳዊ የደከመን አንድ ሰው ለመርዳት አንዳንድ እርምጃዎችን መውሰድ ትችላለህ?
-