የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ‘እርስ በርሳችሁ ፍቅር ይኑራችሁ’
    መጠበቂያ ግንብ—2003 | የካቲት 1
    • 6 ኢየሱስ የተናገረው ሌላው ምሳሌ ስለ አንዲት ሴት ነው። እንዲህ ይላል:- “አሥር ድሪም ያላት አንድ ድሪም ቢጠፋባት፣ መብራት አብርታ ቤትዋንም ጠርጋ እስክታገኘው ድረስ አጥብቃ የማትፈልግ ሴት ማን ናት? ባገኘችውም ጊዜ ወዳጆችዋንና ጐረቤቶችዋን በአንድነት ጠርታ:- የጠፋውን ድሪሜን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ ትላቸዋለች። እላችኋለሁ፣ እንዲሁ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ደስታ ይሆናል።”​—⁠ሉቃስ 15:8-10

  • ‘እርስ በርሳችሁ ፍቅር ይኑራችሁ’
    መጠበቂያ ግንብ—2003 | የካቲት 1
    • ይጥፉ እንጂ ውድ ናቸው

      8. (ሀ) እረኛውና ሴቲቱ የጠፋባቸው ንብረት እንዳለ ሲያውቁ ምን አደረጉ? (ለ) የጠፋባቸውን ፈልገው ለማግኘት የወሰዱት እርምጃ ለንብረቱ ያላቸውን አመለካከት የሚገልጽልን እንዴት ነው?

      8 በሁለቱም ምሳሌዎች ውስጥ አንድ ነገር እንደጠፋ ተገልጿል፤ ሆኖም ባለቤቶቹ ምን እንዳደረጉ ልብ በል። እረኛው ‘99ኙ እስካሉልኝ ድረስ ለአንዱ ምን አስጨነቀኝ? አንዱ ቢጠፋ ምንም አያጎድለኝም’ አላለም። ሴትየዋም ‘ለአንዲት ድሪም ምን አስጨነቀኝ? ዘጠኝ ድሪም ካለኝ ይበቃኛል’ አላለችም። ከዚህ ይልቅ እረኛው አንድ በግ ብቻ ያለው ይመስል የጠፋውን ለማግኘት ፍለጋውን ተያያዘው። ሴትየዋም ከዚያ ሌላ ድሪም የሌላት ይመስል መጥፋቱ በጣም ቆጭቷታል። በሁለቱም ምሳሌዎች ውስጥ ባለቤቶቹ ውድ የሆነ ነገር እንደጠፋባቸው ተሰምቷቸዋል። ይህ ምን ያስተምረናል?

  • ‘እርስ በርሳችሁ ፍቅር ይኑራችሁ’
    መጠበቂያ ግንብ—2003 | የካቲት 1
    • 9. እረኛውና ሴትየዋ ለጠፋባቸው ንብረት የሰጡት ትኩረት የምን ምሳሌ ነው?

      9 ኢየሱስ እያንዳንዱን ምሳሌ ተናግሮ ካበቃ በኋላ “እንዲሁ . . . ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል” እና ‘እንዲሁ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ደስታ ይሆናል’ እንዳለ ልብ በል። እረኛውና ሴትየዋ ለጠፋባቸው ንብረት የሰጡት ትኩረት ይሖዋና ሰማያዊ ፍጥረታቱ ምን እንደሚሰማቸው በመጠኑም ቢሆን ያሳያል። የጠፋው ነገር ለእረኛውም ሆነ ለሴትየዋ ውድ እንደሆነ ሁሉ ባዝነው ከሕዝቦቹ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ያቋረጡ ሰዎችም በይሖዋ ፊት ውድ ናቸው። (ኤርምያስ 31:​3) እንደዚህ ያሉ ግለሰቦች በመንፈሳዊ ተዳክመው ይሆናል፤ ዓመፀኞች ናቸው ማለት ግን አይደለም። በመንፈሳዊ ይድከሙ እንጂ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ይሖዋ ያወጣቸውን መስፈርቶች ይጠብቁ ይሆናል። (መዝሙር 119: 176፤ ሥራ 15:​28, 29) በመሆኑም ይሖዋ ከዚህ በፊትም እንዳደረገው ሁሉ ወዲያውኑ “ከፊቱ አልጣላቸውም።”​—⁠2 ነገሥት 13:​23

      10, 11. (ሀ) ከጉባኤ የጠፉ ሰዎችን እንዴት ልንመለከታቸው ይገባል? (ለ) ኢየሱስ በተናገራቸው ሁለት ምሳሌዎች መሠረት አሳቢነታችንን ልንገልጽላቸው የምንችለው እንዴት ነው?

      10 እንደ ይሖዋና እንደ ኢየሱስ ሁሉ እኛም በመንፈሳዊ ለደከሙትና ከክርስቲያን ጉባኤ ለጠፉት ሰዎች ከልብ እናስባለን። (ሕዝቅኤል 34:​16፤ ሉቃስ 19:​10) በመንፈሳዊ የደከመን ሰው እንደጠፋ በግ እንጂ የመመለስ ተስፋ እንደሌለው አድርገን ማየት አይኖርብንም። ‘ስለ ደከመ ሰው ምን አሳሰበኝ? የእርሱ መኖር አለመኖር በጉባኤው ላይ የሚያመጣው ለውጥ የለም’ ብለን ማሰብ አይኖርብንም። ከዚህ ይልቅ የጠፉትን ሆኖም መመለስ የሚፈልጉትን ሰዎች ይሖዋ እነርሱን በሚያይበት መንገድ ይኸውም ውድ እንደሆኑ አድርገን እንመለከታቸዋለን።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ