የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “ይሖዋ፣ መሐሪና ሞገስ ያለው አምላክ”
    መጠበቂያ ግንብ—1998 | ጥቅምት 1
    • 9, 10. (ሀ) አባካኙ ልጅ ምን የሁኔታዎች ለውጥ አጋጥሞት ነበር? ምንስ እርምጃ ወሰደ? (ለ) በተመሳሳይም በዛሬው ጊዜ እውነተኛውን አምልኮ ትተው የሚወጡ አንዳንዶች ምን ዓይነት መጥፎ ሁኔታ ውስጥ እንደሚወድቁ በምሳሌ አስረዳ።

      9 “ሁሉንም ከከሰረ በኋላ በዚያች አገር ጽኑ ራብ ሆነ፣ እርሱም ይጨነቅ ጀመር። ሄዶም ከዚያች አገር ሰዎች ከአንዱ ጋር ተዳበለ፣ እርሱም እሪያ ሊያሰማራ ወደ ሜዳ ሰደደው። እሪያዎችም ከሚበሉት አሰር ሊጠግብ ይመኝ ነበር፣ የሚሰጠውም አልነበረም።”​—⁠ሉቃስ 15:​14-16

  • “ይሖዋ፣ መሐሪና ሞገስ ያለው አምላክ”
    መጠበቂያ ግንብ—1998 | ጥቅምት 1
    • 11. የአባካኙን ልጅ ችግር ይበልጥ ያባባሰበት ምን ነበር? በዛሬው ጊዜ አንዳንዶች ዓለም የሚያቀርባቸው መስህቦች ‘ከንቱ ማታለያዎች’ ሆነው ያገኟቸውስ እንዴት ነው?

      11 አባካኙ ልጅ ‘ምንም ነገር የሚሰጠው ሰው’ ማጣቱ ችግሩን አባብሶበታል። አዲስ ያፈራቸው ወዳጆቹ የት ደረሱ? አሁንማ ቤሳ ቤስቲን የሌለው ድሃ ስለሆነ ‘ማን ይፈልገዋል።’ (ምሳሌ 14:​20) በተመሳሳይም በዛሬው ጊዜ ከእምነት የሚወጡ ብዙዎች የዚህ ዓለም መስህቦችና አመለካከቶች ‘ከንቱ ማታለያዎች’ ሆነው ያገኟቸዋል። (ቆላስይስ 2:​8) ለተወሰነ ጊዜ ከአምላክ ድርጅት ወጥታ የነበረች አንዲት ወጣት “ከይሖዋ አመራር በመራቄ ብዙ መከራና ሐዘን ደርሶብኛል” ስትል ተናግራለች። “ከዓለም ጋር ተመሳስዬ ለመኖር ጥረት አድርጌ ነበር፤ ሆኖም ሙሉ በሙሉ እነሱን መምሰል ስላልቻልኩ ገሸሽ አደረጉኝ። የሚመራው አባት እንደሚፈልግ የጠፋ ልጅ የሆንኩ ያህል ተሰምቶኝ ነበር። ይሖዋ እንደሚያስፈልገኝ የተገነዘብኩት በዚህ ጊዜ ነው። ከዚያን ጊዜ ወዲህ ከይሖዋ ተለይቶ መኖርን እርም አልኩኝ።” በኢየሱስ ምሳሌ ላይ የተጠቀሰው አባካኝ ልጅ ተመሳሳይ ወደሆነ ግንዛቤ ደርሷል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ