የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ጠፍቶ የነበረው ልጅ ተመለሰ
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
    • አባት ታላቅየውን ልጅ ሲያነጋግር

      በዚህ ጊዜ ታላቁ ልጅ ያለው በእርሻ ቦታ ነው። ኢየሱስ ስለ እሱ ሲናገር እንዲህ አለ፦ “ተመልሶ መጥቶ ወደ ቤት በተቃረበ ጊዜ የሙዚቃና የጭፈራ ድምፅ ሰማ። ስለዚህ ከአገልጋዮቹ አንዱን ጠርቶ ነገሩ ምን እንደሆነ ጠየቀው። አገልጋዩም ‘ወንድምህ መጥቷል፤ በደህና ስለመጣም አባትህ የሰባውን ጥጃ አርዶለታል’ አለው። እሱ ግን ተቆጣ፤ ወደ ቤት ለመግባትም አሻፈረኝ አለ። ከዚያም አባቱ ወጥቶ ይለምነው ጀመር። እሱም መልሶ አባቱን እንዲህ አለው፦ ‘እነሆ፣ እኔ ስንት ዓመት ሙሉ እንደ ባሪያ ሳገለግልህ ኖርኩ፤ መቼም ቢሆን ከትእዛዝህ ዝንፍ ብዬ አላውቅም፤ አንተ ግን ከጓደኞቼ ጋር እንድደሰት አንዲት የፍየል ጠቦት እንኳ ሰጥተኸኝ አታውቅም። ሆኖም ሀብትህን ከዝሙት አዳሪዎች ጋር ያወደመው ይህ ልጅህ ገና ከመምጣቱ የሰባውን ጥጃ አረድክለት።’”—ሉቃስ 15:25-30

      ኢየሱስ ለተራው ሕዝብና ለኃጢአተኞች ምሕረት በማሳየቱና ትኩረት በመስጠቱ ልክ እንደ ታላቁ ልጅ የነቀፉት እነማን ናቸው? ጸሐፍትና ፈሪሳውያን አይደሉም? ኢየሱስ ይህን ምሳሌ ለመናገር የተነሳሳው ኃጢአተኞችን በመቀበሉ ትችት ስለሰነዘሩበት ነው። በእርግጥም አምላክ ምሕረት በማሳየቱ ቅር የሚሰኙ ሁሉ ከዚህ ምሳሌ ትምህርት ሊያገኙ ይገባል።

  • ጠፍቶ የነበረው ልጅ ተመለሰ
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
    • ኢየሱስ፣ ታላቁ ልጅ በመጨረሻ ምን እንዳደረገ አልገለጸም። ሆኖም ኢየሱስ ከሞት ከተነሳ በኋላ ‘ብዙ ካህናት ይህን እምነት ተቀብለዋል።’ (የሐዋርያት ሥራ 6:7) ከእነዚህም መካከል ኢየሱስ፣ ጠፍቶ ስለነበረው ልጅ የተናገረውን ይህን ልብ የሚነካ ምሳሌ ከሰሙት አንዳንዶቹ ይገኙበት ይሆናል። እነሱም እንኳ ወደ ልቦናቸው ተመልሰው ንስሐ በመግባት ከአምላክ ጋር ያላቸውን ዝምድና አድሰው ሊሆን ይችላል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ