-
“በልቧ ይዛ ታሰላስል ነበር”መጠበቂያ ግንብ—2008 | ጥቅምት 1
-
-
ዮሴፍና ማርያም እዚያ ሲደርሱ መንደሯ በሰው ተጥለቅልቃ ነበር። ሌሎች ሰዎች ለመመዝገብ ከእነሱ ቀደም ብለው ወደ ከተማዋ መጥተው ስለነበር ለማረፊያ የሚሆን ቦታ አልነበረም።b በመሆኑም በጋጣ ውስጥ ከማደር በስተቀር ሌላ አማራጭ አልነበራቸውም። ዮሴፍ፣ ሚስቱ ከዚህ በፊት ተሰምቷት የማያውቅ ሥቃይ እየበረታባት ሲሄድ መመልከቱ ምን ያህል አስጨንቆት ሊሆን እንደሚችል መገመት አያዳግትም። ምንም በማያመቸው በዚህ ስፍራ ማርያም ምጥ ጀመራት!
በየትኛውም አካባቢ የሚገኙ ሴቶች ማርያም የነበረችበትን ሁኔታ መረዳት አይከብዳቸውም። ይህ ከመሆኑ ከ4,000 ዓመታት ገደማ በፊት ይሖዋ፣ ሰዎች በወረሱት ኃጢአት ምክንያት በሚወልዱበት ጊዜ እንደሚሠቃዩ ተናግሯል። (ዘፍጥረት 3:16) ማርያም እንዲህ ያለው ሥቃይ እንዳልደረሰባት የተገለጸ ነገር የለም። የሉቃስ ዘገባ፣ ማርያም ስላጋጠማት ሥቃይ ከመግለጽ ይልቅ “የበኵር ልጇ የሆነውን ወንድ ልጅ ወለደች” በማለት በአጭሩ ይናገራል። (ሉቃስ 2:7) ማርያም ከወለደቻቸው ቢያንስ ሰባት ልጆች መካከል “የበኵር” ልጇን ወለደች። (ማርቆስ 6:3) ይህ ልጅ ግን ከሌሎቹ ፈጽሞ የተለየ ነበር። ይህ ልጅ የማርያም የበኵር ልጅ ብቻ ሳይሆን ከይሖዋ “ፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር” የሆነ የአምላክ አንድያ ልጅ ነው!—ቈላስይስ 1:15
የሉቃስ ዘገባ በመቀጠል በብዙ ሰዎች ዘንድ የሚታወቀውን ማርያም ያደረገችውን አንድ ክንውን ሲገልጽ ‘[ሕፃኑን] በጨርቅ ጠቅልላ በግርግም አስተኛችው’ በማለት ይናገራል። (ሉቃስ 2:7) የክርስቶስን ልደት አስመልክቶ የሚቀርቡ ድራማዎች፣ ሥዕሎችና ሌሎች ትዕይንቶች ይህን ክንውን ከመጠን በላይ ማራኪ በማድረግ ከእውነታው በራቀ መንገድ ሲያቀርቡት ይስተዋላል። ይሁን እንጂ በወቅቱ ምን እንደተከሰተ ተመልከት። ግርግም፣ ከብቶች የሚመገቡበት ገንዳ ነው። ዮሴፍና ማርያም ያረፉት በዛሬው ጊዜ እንደሚታየው ንጹሕ አየር እንደልብ በማይገኝበት ወይም ንጽሕና በሌለው ጋጣ ውስጥ ነበር። ማንም ወላጅ ቢሆን አማራጭ ካላጣ በስተቀር እንዲህ ባለው ስፍራ ላይ ልጅ መውለድ እንደማይፈልግ ግልጽ ነው። አብዛኞቹ ወላጆች ለልጆቻቸው ከሁሉ የተሻለውን ነገር ማድረግ ይፈልጋሉ። በመሆኑም ማርያምና ዮሴፍ ለአምላክ ልጅ ይበልጥ የተሻለውን ለማድረግ የቻሉትን ሁሉ ጥረው እንደነበር ምንም ጥርጥር የለውም!
ይሁን እንጂ ዮሴፍና ማርያም በገጠማቸው ሁኔታ ከመማረር ይልቅ ከሁሉ የተሻለውን ለማድረግ አቅማቸው የሚፈቅደውን ሁሉ አድርገዋል። ለምሳሌ ያህል፣ ማርያም ሕፃኑን እንዲሞቀውና ጉዳት እንዳይደርስበት በጨርቅ ጠቅልላ በጥንቃቄ ግርግም ውስጥ በማስተኛት እንደተንከባከበችው ልብ በል። ማርያም ሁኔታው ከልክ በላይ እንዲያስጨንቃት ከመፍቀድ ይልቅ ለልጇ የቻለችውን ሁሉ አድርጋለች። ማርያምና ዮሴፍ ለልጃቸው ሊሰጡት የሚችሉት ከሁሉ የላቀ ነገር መንፈሳዊ እንክብካቤ ማድረግ መሆኑን ተገንዝበው ነበር። (ዘዳግም 6:6-8) በዛሬው ጊዜም ጥበበኛ የሆኑ ወላጆች ለመንፈሳዊ ነገሮች ቦታ በማይሰጥ ዓለም ውስጥ ልጆቻቸውን ሲያሳድጉ ይበልጥ አስፈላጊ ለሆነው ነገር ቅድሚያ ይሰጣሉ።
-
-
“በልቧ ይዛ ታሰላስል ነበር”መጠበቂያ ግንብ—2008 | ጥቅምት 1
-
-
b በወቅቱ የከተማዋ ሰዎች ለመንገደኞች የማረፊያ ቦታ ማዘጋጀታቸው የተለመደ ነበር።
-