-
የሀብታሙ ሰውና የአልዓዛር ሁኔታ ተለወጠኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
-
-
የሙሴ ሕግ ሳይፈጸም አልቀረም፤ እንዲያውም ሕዝቡን ወደ መሲሑ መርቷል። ሆኖም ሕጉን መጠበቅ ግዴታ መሆኑ ሊቀር ነው። ለምሳሌ ያህል፣ ሕጉ በተለያዩ ምክንያቶች ፍቺን ይፈቅዳል፤ አሁን ግን ኢየሱስ “ሚስቱን ፈቶ ሌላ የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል፤ ባሏ የፈታትንም ሴት የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል” በማለት ተናገረ። (ሉቃስ 16:18) ይህ ሐሳብ፣ ለሁሉ ነገር ሕግ ማውጣት የሚወዱትን ፈሪሳውያን ምንኛ አበሳጭቷቸው ይሆን!
-