-
የአምላክ መንግሥት በሰዎች ልብ ውስጥ ያለ ነገር ነው?የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
-
-
ኢየሱስ “የአምላክ መንግሥት በውስጣችሁ ነው” ሲል ምን ማለቱ ነበር?
አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች (ለምሳሌ፣ ኪንግ ጄምስ ቨርዥን) ሉቃስ 17:21ን “የአምላክ መንግሥት በውስጣችሁ ነው” በማለት አስቀምጠውታል። በመሆኑም አንዳንድ ሰዎች ይህ ሐሳብ የአምላክ መንግሥት ስለሚገኝበት ቦታ ግራ እንዲጋቡ አድርጓቸዋል። ይህን ጥቅስ በትክክል ለመረዳት በመጀመሪያ የጥቅሱን ዐውድ እንመልከት።
የአምላክ መንግሥት ዓመፀኛና ነፍሰ ገዳይ በሆኑት የኢየሱስ ተቃዋሚዎች ልብ ውስጥ ሊገኝ አይችልም
ኢየሱስ ይህን ሐሳብ የተናገረው ለፈሪሳውያን ነው፤ ፈሪሳውያን ደግሞ ኢየሱስን የሚቃወሙና እሱን ለማጥፋት እያሴሩ የነበሩ የሃይማኖት መሪዎች ናቸው። (ማቴዎስ 12:14፤ ሉቃስ 17:20) ታዲያ የአምላክ መንግሥት በእነዚህ ዓመፀኛ ሰዎች ልብ ውስጥ ያለውን ሁኔታ የሚያመለክት ሊሆን ይችላል? ኢየሱስ ፈሪሳውያንን “ውስጣችሁ . . . በግብዝነትና በዓመፅ የተሞላ ነው” ብሏቸዋል።—ማቴዎስ 23:27, 28
በሉቃስ 17:21 ላይ የሚገኘውን የኢየሱስ ሐሳብ በትክክል ያስቀመጡ በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች አሉ፦ “የእግዚአብሔር መንግሥት በመካከላችሁ ናት።” (በሰያፍ የጻፍነው እኛ ነን፤ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) “የአምላክ መንግሥት በመካከላችሁ ነው።” (አዲስ ዓለም ትርጉም) መንግሥተ ሰማያት በፈሪሳውያን ‘መካከል’ እንደሆነ የተገለጸው የዚህ መንግሥት ንጉሥ እንዲሆን በአምላክ የተሾመው ኢየሱስ በመካከላቸው ቆሞ ስለነበር ነው።—ሉቃስ 1:32, 33
-
-
የአምላክ መንግሥት በሰዎች ልብ ውስጥ ያለ ነገር ነው?የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
-
-
a ብዙ የክርስትና ሃይማኖቶች፣ የአምላክ መንግሥት በአንድ ግለሰብ ውስጥ ወይም በልቡ ውስጥ የሚገኝ ነገር እንደሆነ ያስተምራሉ። ለምሳሌ ያህል በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኝ አንድ የክርስትና ሃይማኖት፣ የአምላክ መንግሥት በአንድ በኩል “አምላክ በአንድ ሰው ልብና ሕይወት ላይ መንገሡን የሚያመለክት ሁኔታ” እንደሆነ ያስተምራል። በተመሳሳይም የሮም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የሆኑት ቤነዲክት 16ኛ፣ የናዝሬቱ ኢየሱስ (እንግሊዝኛ) በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ “የአምላክ መንግሥት የሚመጣው ታዛዥ በሆነ ልብ በኩል ነው” በማለት ገልጸዋል።
-