የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ይሖዋ ‘ይፈርዳል’
    መጠበቂያ ግንብ—2006 | ታኅሣሥ 15
    • 8 ኢየሱስ ይህን ካላቸው በኋላ ይህ ምሳሌ እንዴት በሥራ ላይ እንደሚውል ሲናገር እንዲህ አለ:- “ዐመፀኛው ዳኛ ያለውን ስሙ። እግዚአብሔርስ ቀንና ሌሊት ወደ እርሱ ለሚጮኹ ምርጦቹ አይፈርድላቸውምን? ከመጠን በላይስ ችላ ይላቸዋልን? እላችኋለሁ፤ ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል፤ ነገር ግን የሰው ልጅ በሚመጣበት ጊዜ በምድር ላይ እምነትን ያገኝ ይሆንን?”—ሉቃስ 18:1-8

  • ይሖዋ ‘ይፈርዳል’
    መጠበቂያ ግንብ—2006 | ታኅሣሥ 15
    • 9. ስለ መበለቲቱና ስለ ዳኛው በተነገረው ምሳሌ ላይ ጎልቶ የወጣው ጭብጥ ምንድን ነው?

      9 የዚህ ሕያው ምሳሌ ዋነኛ ጭብጥ በጣም ግልጽ ነው። ጭብጡ በኢየሱስ ንግግርም ሆነ በምሳሌው ውስጥ በተጠቀሱት ሰዎች ባሕርይ ላይ ተንጸባርቋል። መበለቲቱ “ፍረድልኝ” ስትል ተማጽናለች። ዳኛው ደግሞ “እፈርድላታለሁ” ብሏል። ኢየሱስም “እግዚአብሔርስ . . . ወደ እርሱ ለሚጮኹ ምርጦቹ አይፈርድላቸውምን?” ሲል ጠይቋል። ከዚያም ይሖዋን በሚመለከት “ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል” በማለት ተናግሯል። (ሉቃስ 18:3, 5, 7, 8) ታዲያ ይሖዋ ‘የሚፈርደው’ መቼ ነው?

      10. (ሀ) በመጀመሪያው መቶ ዘመን ፍርድ የተሰጠው መቼ ነው? (ለ) በአሁኑ ጊዜ ለሚኖሩ የአምላክ አገልጋዮች የሚፈረድላቸው መቼና እንዴት ነው?

      10 በመጀመሪያው መቶ ዘመን “የበቀል ጊዜ” የመጣው በ70 ከክርስቶስ ልደት በኋላ ኢየሩሳሌምና በውስጧ ያለው ቤተ መቅደስ በጠፋበት ወቅት ነበር። (ሉቃስ 21:22) በአሁን ጊዜ ላሉት የአምላክ ሕዝቦች የሚፈረድላቸው ‘በታላቁ የይሖዋ ቀን’ ነው። (ሶፎንያስ 1:14፤ ማቴዎስ 24:21) በዚያን ጊዜ ይሖዋ በሕዝቡ ላይ ‘መከራን ለሚያመጡ መከራን የሚከፍላቸው’ ሲሆን ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ “እግዚአብሔርን የማያውቁትንና ለጌታችንም ለኢየሱስ ወንጌል የማይታዘዙትን ይበቀላል።”—2 ተሰሎንቄ 1:6-8፤ ሮሜ 12:19

  • ይሖዋ ‘ይፈርዳል’
    መጠበቂያ ግንብ—2006 | ታኅሣሥ 15
    • 12, 13. (ሀ) ኢየሱስ ስለ መበለቲቱና ስለ ዳኛው በተናገረው ምሳሌ ላይ ትምህርቱን ያቀረበው እንዴት ነው? (ለ) ይሖዋ ጸሎታችንን እንደሚሰማና እንደሚፈርድልን እርግጠኞች መሆን የምንችለው ለምንድን ነው?

      12 ስለ መበለቲቱና ስለ ዳኛው የሚገልጸው ምሳሌ ሌሎች አስፈላጊ እውነቶችንም ጎላ አድርጎ ይገልጻል። ኢየሱስ የምሳሌውን ተግባራዊ ጠቀሜታ በተናገረ ጊዜ “ዐመፀኛው ዳኛ ያለውን ስሙ። እግዚአብሔርስ ቀንና ሌሊት ወደ እርሱ ለሚጮኹ ምርጦቹ አይፈርድላቸውምን?” ብሏል። እርግጥ ነው ኢየሱስ በምሳሌው ላይ ይሖዋን ከዳኛው ጋር ያወዳደረው አምላክ በእርሱ የሚያምኑትን ሰዎች በተመሳሳይ መንገድ ይይዛቸዋል ለማለት አይደለም። ከዚህ ይልቅ ኢየሱስ፣ በዳኛውና በአምላክ መካከል ያሉትን ልዩነቶች በማነጻጸር ደቀ መዛሙርቱን ስለ ይሖዋ አስተምሯቸዋል። በዳኛውና በአምላክ መካከል ያሉት ልዩነቶች ምንድን ናቸው?

      13 በኢየሱስ ምሳሌ ላይ የተጠቀሰው ዳኛ “ዐመፀኛ” ሲሆን ‘አምላክ ግን ጻድቅ ዳኛ ነው።’ (መዝሙር 7:11፤ 33:5) ዳኛው ለመበለቲቱ በግለሰብ ደረጃ አላሰበላትም፤ ይሖዋ ግን የእያንዳንዱ ግለሰብ ሁኔታ ያሳስበዋል። (2 ዜና መዋዕል 6:29, 30) ዳኛው መበለቲቱን ለመርዳት ፈቃደኛ አልነበረም፤ ይሖዋ ግን አገልጋዮቹን ለመርዳት ፈቃደኛና ዝግጁ ነው። (ኢሳይያስ 30:18, 19) ከዚህ ምን ትምህርት እናገኛለን? ዓመጸኛው ዳኛ የመበለቲቱን ልመና ሰምቶ ከፈረደላት ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ይሖዋ የሕዝቦቹን ጸሎት እንደሚሰማና እንደሚፈርድላቸው ምንም ጥርጥር የለውም!—ምሳሌ 15:29

      14. በመጪው የአምላክ የፍርድ ቀን ላይ እምነት ማጣት የሌለብን ለምንድን ነው?

      14 በመሆኑም በመጪው የአምላክ የፍርድ ቀን ላይ ያላቸውን እምነት ያጡ ሰዎች ከባድ ስሕተት ሠርተዋል። ለምን? ‘ታላቁ የይሖዋ ቀን’ ቅርብ ስለመሆኑ ያላቸውን ጽኑ እምነት በማላላት ይሖዋ ቃሉን በታማኝነት በመጠበቁ ላይ ጥያቄ እንዳላቸው በተግባራቸው አሳይተዋል። ይሁንና ማንም ሰው ቢሆን ስለ አምላክ ታማኝነት ጥያቄ የማንሳት መብት የለውም። (ኢዮብ 9:12) ልናስብበት የሚገባን ተገቢ ጥያቄ ‘እያንዳንዳችን በግለሰብ ደረጃ ታማኝ እንሆናለን?’ የሚለው ነው። ኢየሱስም ስለ መበለቲቱና ስለ ዳኛው በተናገረው ምሳሌ መደምደሚያ ላይ ያነሳው ነጥብ ይህ ነው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ