የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • እምነት ልትጥልበት የምትችል መጽሐፍ​—ክፍል 6
    ንቁ!—2011 | ሚያዝያ
    • መጽሐፍ ቅዱስ በሮማውያን ዘመን ተጽፈው በዚያው ዘመን ፍጻሜያቸውን ያገኙ አስገራሚ ትንቢቶችንም ይዟል። ለምሳሌ ኢየሱስ በውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም በገባበት ጊዜ ስለዚህች ከተማ ያለቀሰ ከመሆኑም ሌላ የሮማውያን ሠራዊት እንዴት እንደሚያጠፋት ትንቢት ተናግሯል። ኢየሱስ “ጠላቶችሽ በሾለ እንጨት ዙሪያሽን ቅጥር ቀጥረው . . . አንቺን የሚያስጨንቁበት ጊዜ ይመጣል” ብሏል። አክሎም “በአንቺ ውስጥም ሳያፈርሱ እንደተነባበረ የሚተዉት ድንጋይ አይኖርም፤ ምክንያቱም በአንቺ ላይ ምርመራ የሚካሄድበትን ጊዜ አልተገነዘብሽም” ሲል ተንብዮአል።​—ሉቃስ 19:41-44

  • እምነት ልትጥልበት የምትችል መጽሐፍ​—ክፍል 6
    ንቁ!—2011 | ሚያዝያ
    • [በገጽ 13 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

      በሮም የሚገኘው የቲቶ ቅስት በ70 ዓ.ም. ኢየሩሳሌም ለመጥፋቷ መታሰቢያ ነው

      ቲቶ በኢየሩሳሌም ያለው ቤተ መቅደስ እንዳይነካ አዝዞ የነበረ ቢሆንም አንድ ወታደር እሳት ስለለኮሰበት ሙሉ በሙሉ ወደመ፤ ልክ ኢየሱስ እንደተነበየው ሳይፈርስ እንደተነባበረ የቀረ ድንጋይ አልነበረም። ጆሴፈስ እንደዘገበው 1,100,000 የሚያህሉ አይሁዳውያንና ወደ አይሁድ እምነት የተለወጡ ሰዎች አለቁ፤ አብዛኞቹ የሞቱት በረሃብና በቸነፈር ምክንያት ነው። ከእነዚህ ሌላ 97,000 የሚያህሉ ደግሞ በግዞት ተወሰዱ። ብዙዎች በባርነት ወደ ሮም ተላኩ። ዛሬ ሮምን ብትጎበኝ ቲቶ በይሁዳ ላይ ከዘመተ በኋላ ያጠናቀቀውን ዝነኛውን ኮሎሲየም ማየት ትችላለህ። በተጨማሪም ቲቶ ኢየሩሳሌምን ድል በማድረጉ ለመታሰቢያነት የቆመውን የቲቶ ቅስት መመልከት ትችላለህ። አዎን፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት በዝርዝር ጉዳዮች እንኳ ሳይቀር እምነት የሚጣልበት ነው። እንግዲያው መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ወደፊቱ ጊዜ ለሚናገረው ትንቢት ትኩረት መስጠታችን ምንኛ አስፈላጊ ነው!

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ