የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የምትታዘዘው አምላክን ነው ወይስ ሰውን?
    መጠበቂያ ግንብ—2005 | ታኅሣሥ 15
    • 7. የስብከቱ ሥራ የካህናት አለቆችን ያስቆጣቸው ለምን ነበር?

      7 ሐዋርያት መስበካቸውን ለመቀጠል ያደረጉት ቁርጥ ውሳኔ የካህናት አለቆቹን አስቆጣቸው። ቀያፋን ጨምሮ ከካህናት አለቆች አንዳንዶቹ ሰዱቃውያን ስለሆኑ በትንሣኤ አያምኑም ነበር። (የሐዋርያት ሥራ 4:1, 2፤ 5:17) ሐዋርያት ግን ኢየሱስ ከሞት መነሳቱን አስረግጠው እየተናገሩ ናቸው። ከዚህም በላይ ከካህናት አለቆች አንዳንዶቹ በሮም ባለ ሥልጣናት ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት ሲሉ ብዙ ደክመዋል። ኢየሱስ ለፍርድ ቀርቦ በነበረበት ወቅት እርሱን ንጉሣቸው አድርገው የመቀበል አጋጣሚ ሲቀርብላቸው የካህናት አለቆች “ከቄሣር በቀር ሌላ ንጉሥ የለንም” ብለው እስከመናገር ደርሰው ነበር። (ዮሐንስ 19:15)a ሐዋርያት ደግሞ ኢየሱስ ትንሣኤ ማግኘቱን በእርግጠኝነት ከመናገርም አልፈው “እንድንበት ዘንድ ለሰዎች የተሰጠ [ከኢየሱስ] ስም በስተቀር ሌላ ስም ከሰማይ በታች የለም” ብለው እያስተማሩ ነው። (የሐዋርያት ሥራ 2:36፤ 4:12) ካህናቱ፣ ሕዝቡ ከሞት የተነሳው ኢየሱስን መሪያቸው አድርገው መመልከት ከጀመሩ ሮማውያን መጥተው ‘ሥፍራቸውንና ሕዝባቸውን’ እንዳይወስዱባቸው ፈርተው ነበር።—ዮሐንስ 11:48

  • የምትታዘዘው አምላክን ነው ወይስ ሰውን?
    መጠበቂያ ግንብ—2005 | ታኅሣሥ 15
    • a የካህናት አለቆች በዚህ ወቅት በሕዝቡ ፊት የደገፉት “ቄሣር” የተጠላው የሮም ንጉሠ ነገሥት ጢባሪዮስ ነው። ይህ ሰው ግብዝና ነፍሰ ገዳይ ከመሆኑም በላይ ርካሽ የጾታ ድርጊቶች በመፈጸም የታወቀ ነበር።—ዳንኤል 11:15, 21

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ