የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w91 4/15 ገጽ 8-9
  • በገሊላ ባሕር

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በገሊላ ባሕር
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በገሊላ ባሕር
    እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው
  • በገሊላ ባሕር ዳርቻ
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ በድጋሚ ታየ
    ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • ፍርሃትንና ጥርጣሬን ለማሸነፍ ታግሏል
    በእምነታቸው ምሰሏቸው
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
w91 4/15 ገጽ 8-9

ኢየሱስ ሕይወቱና አገልግሎቱ

በገሊላ ባሕር

አሁን ሐዋርያት ኢየሱስ ቀደም ሲል የነገራቸውን በመከተል ወደ ገሊላ ተመለሱ። ይሁን እንጂ እዚያ ሄደው ምን እንደሚሠሩ እርግጠኞች አልነበሩም። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ጴጥሮስ ለቶማስ፣ ለናትናኤል፣ ለያዕቆብና ለያዕቆብ ወንድም ለዮሐንስ እንዲሁም ለሌሎች ሁለት ሐዋርያት “ዓሣ ላጠምድ እሄዳለሁ” አላቸው።

ስድስቱም፦ “ከአንተ ጋር እንመጣለን” ብለው መለሱለት።

ሌሊቱን በሙሉ ምንም ዓሣ ሳይዙ ቀሩ። ሆኖም ሲነጋጋ ኢየሱስ በወንዙ ዳር ተገለጠ፣ ሐዋርያት ግን ኢየሱስ እንደሆነ አላወቁትም። እርሱም ጮክ ብሎ “ልጆች ሆይ፣ የሚበላ አላችሁን?” አላቸው።

“የለንም!” ብለው ውሃው ውስጥ እንዳሉ መለሱለት።

“እርሱም፦ መረቡን በታንኳይቱ በስተ ቀኝ ጣሉት ታገኙማላችሁ አላቸው።” ይህንን ሲያደርጉም ከዓሣው ብዛት የተነሣ መረባቸውን መጎተት አቃታቸው። ዮሐንስ “ጌታ እኮ ነው!” ብሎ ጮኸ። ጴጥሮስ ልብሱን ለብሶ ወደ ባሕር ጠለቀ። ወደ ባሕሩ ዳር ለመድረስም ወደ መቶ ሜትር ያህል ዋኘ። ሌሎቹ ሐዋርያት በዓሣ የተሞላውን መረብ እየሳቡ በትንሽ ጀልባ ተከተሉት።

ወደ ምድር ሲወጡም የከሰል እሳትና በላዩ ላይ ዓሣ ተቀምጦ ከዳቦ ጋር አዩ። ኢየሱስም “አሁን ካጠመዳችሁት ዓሣ አምጡ” አላቸው። ጴጥሮስ ሄዶ መረቡን ወደ ምድር ሳበው። 153 ትልልቅ ዓሦችን ይዞ ነበር!

ኢየሱስም “ኑ ቁርሳችሁን ብሉ” ሲል ጋበዛቸው።

ከእነርሱ ውስጥ ማንም “አንተ ማነህ?” ብሎ ለመጠየቅ የደፈረ አልነበረም። ምክንያቱም ሁሉም ኢየሱስ መሆኑን አውቀው ነበር። ይህ ከትንሣኤው በኋላ ለሰባተኛ ጊዜ የተገለጠበት ሲሆን ለሐዋርያት ደግሞ በቡድን ለሦስተኛ ጊዜ የተገለጠበት ወቅት ነው። አሁን ለእያንዳንዳቸው ዳቦና ዓሣ በመስጠት ቁርስ እያበላቸው ነው።

መብላት በጨረሱ ጊዜ ምናልባት ኢየሱስ ወደተያዙት ዓሦች በራሱ እያመለከተ ጴጥሮስን፦ “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፣ ከእነዚህ ይልቅ ትወደኛለህን?” ሲል ጠየቀው። ምናልባት ከዓሣ ማጥመዱ ሥራ ይልቅ እኔ እንድትሠራው ካዘጋጀሁህ ሥራ ጋር ትጣበቃለህን? ማለቱ ሊሆን ይችላል።

ጴጥሮስም “እንደምወድህ አንተ ታውቃለህ” ብሎ መለሰለት።

ኢየሱስም “ግልገሎቼን አሠማራ” አለው።

ደግሞም ሁለተኛ ጊዜ “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፣ ትወደኛለህን?” ብሎ ጠየቀው።

“አዎን ጌታ ሆይ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ” ብሎ ጴጥሮስ መለሰለት።

“ጠቦቶቼን ጠብቅ” በማለት ኢየሱስ እንደገና አዘዘው።

አሁንም እንደገና ለሦስተኛ ጊዜ “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ ትወደኛለህን?” ብሎ ጠየቀው።

በዚህን ጊዜ ጴጥሮስ አዘነ። ኢየሱስ የእርሱን ታማኝነት እንደተጠራጠረው አድርጎ አስቦ ሊሆን ይችላል። እንዲያውም ኢየሱስ በቅርቡ ሞት ሊፈረድበት ፍርድ ላይ በነበረበት ጊዜ ጴጥሮስ አላውቀውም በማለት ሦስት ጊዜ ክዶት ነበር። ስለዚህ ጴጥሮስ “ጌታ ሆይ፣ አንተ ሁሉን ታውቃለህ፤ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ” አለው።

ኢየሱስ ለሦስተኛ ጊዜ “በጎቼን አሠማራ” በማለት አዘዘው።

እዚህ ላይ ኢየሱስ ሌሎቹም ሐዋርያት እርሱ እንዲሠሩት የሚፈልገውን ሥራ እንዲሠሩ ለመገፋፋት ጴጥሮስን እንደሚያስተጋባ መሣሪያ አድርጎ ተጠቅሞበታል። ኢየሱስ በቅርቡ ምድርን ትቶ ሊሄድ ነው፤ ስለዚህ ወደ አምላክ የበጎች በረት የሚመጡትን ለማገልገል የመሪነቱን ቦታ እንዲይዙ ይፈልግባቸዋል።

ኢየሱስ አምላክ እንዲሠራው የሰጠውን ሥራ በመሥራቱ ምክንያት እንደታሰረና እንደተገደለ ሁሉ ጴጥሮስም ተመሳሳይ ሁኔታ እንደሚያጋጥመው ኢየሱስ ገለጠለት። “አንተ ጎልማሳ ሳለህ” አለ ኢየሱስ “ወገብህን በገዛ ራስህ ታጥቀህ ወደምትወደው ትሄድ ነበር፤ ነገር ግን በሸመገልህ ጊዜ እጆችህን ትዘረጋለህ፣ ሌላውም ያስታጥቅሃል ወደማትወደውም ይወስድሃል።” ጴጥሮስን ሰማዕታዊ ሞት የሚጠብቀው ቢሆንም እንኳ ኢየሱስ “[ሳታቋርጥ (አዓት)] ተከተለኝ” በማለት አሳሰበው።

ጴጥሮስ ዘወር ሲል ዮሐንስን አየውና “ጌታ ሆይ፣ ይህስ እንዴት ይሆናል?” ሲል ጠየቀው።

ኢየሱስም “እስክመጣ ድረስ ይኖር ዘንድ ብወድስ፣ ምን አግዶህ? አንተ ተከተለኝ” አለው።

ብዙዎቹ ደቀመዛሙርት ኢየሱስ የተናገራቸውን እነዚህን ቃላት የተረዱት ሐዋርያው ዮሐንስ ፈጽሞ እንደማይሞት አድርገው ነበር። ሆኖም ሐዋርያው ዮሐንስ በኋላ እንደገለጸው ኢየሱስ ያለው አይሞትም ሳይሆን በአጭሩ፦ “እስክመጣ ድረስ ይኖር ዘንድ ብወድስ ምን አግዶህ?” ነው። ዮሐንስ 21:1-25፤ ማቴዎስ 26:32፤ 28:7, 10

◆ ሐዋርያት በገሊላ ምን ማድረግ እንዳለባቸው እርግጠኞች እንዳልነበሩ የሚያሳየው ምንድን ነው?

◆ ሐዋርያት በገሊላ ባሕር ኢየሱስን ያወቁት እንዴት ነበር?

◆ ኢየሱስ ከትንሣኤው በኋላ ሲገለጥ አሁን ስንተኛ ጊዜው ነው?

◆ ኢየሱስ ሐዋርያቱ እንዲሠሩት የፈለገውን ሥራ ያጎላው እንዴት ነበር?

◆ ኢየሱስ ጴጥሮስ የሚሞትበትን ሁኔታ ያመለከተው እንዴት ነው?

◆ ብዙዎቹ ደቀመዛሙርት ኢየሱስ ስለ ዮሐንስ የሰጠውን የትኛውን አባባል በትክክል አልተረዱም ነበር?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ