-
ቤዛው የሚያድነን እንዴት ነው?መጠበቂያ ግንብ—2010 | ነሐሴ 15
-
-
ከአምላክ ቁጣ መዳን
4, 5. አምላክ በዚህ ክፉ ሥርዓት ላይ አሁንም ድረስ እንደተቆጣ የሚያሳየው ምንድን ነው?
4 መጽሐፍ ቅዱስና የሰው ዘር ታሪክ እንደሚያሳየው አዳም በኃጢአት ከወደቀበት ጊዜ አንስቶ የአምላክ ቁጣ በሰው ልጆች ላይ ነው። (ዮሐ. 3:36) ይዋል ይደር እንጂ ማንኛውም ሰው ከሞት ማምለጥ አለመቻሉ ይህ እውነት መሆኑን ያሳያል። የአምላክ ተቀናቃኝ የሆነው የሰይጣን አገዛዝ የሰው ልጆችን ከሚደርስባቸው ማቆሚያ የሌለው መከራ ፈጽሞ ሊታደጋቸው አልቻለም፤ እንዲሁም የሁሉንም ዜጎቹን መሠረታዊ ፍላጎት ማሟላት የቻለ አንድም ሰብዓዊ መንግሥት የለም። (1 ዮሐ. 5:19) በመሆኑም የሰው ልጅ ከጦርነት፣ ከወንጀልና ከድህነት መላቀቅ አልቻለም።
-
-
ቤዛው የሚያድነን እንዴት ነው?መጠበቂያ ግንብ—2010 | ነሐሴ 15
-
-
7 ሐዋርያው ጳውሎስ፣ ኢየሱስ “ከሚመጣው ቁጣ የሚያድነን” መሆኑን ተናግሯል። (1 ተሰ. 1:10) ይሖዋ ቁጣውን ለመጨረሻ ጊዜ በሚገልጥበት በዚያ ወቅት ንስሐ ያልገቡ ኃጢአተኞች ለዘላለም ይጠፋሉ። (2 ተሰ. 1:6-9) ታዲያ ከዚህ ቁጣ የሚያመልጡት እነማን ናቸው? መጽሐፍ ቅዱስ “በወልድ እንደሚያምን በተግባር የሚያሳይ የዘላለም ሕይወት አለው፤ ወልድን የማይታዘዝ ግን የአምላክ ቁጣ በላዩ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም” ይላል። (ዮሐ. 3:36) አዎን፣ የዚህ ሥርዓት ፍጻሜ በሚመጣበት ጊዜ በሕይወት የሚኖሩ ሁሉ በኢየሱስ ብሎም በቤዛው ላይ እምነት እንዳላቸው በተግባር እስካሳዩ ድረስ መጨረሻ ከሚመጣው የአምላክ የቁጣ ቀን ይተርፋሉ።
-