-
የአምላክ እረፍት ምንድን ነው?መጠበቂያ ግንብ—2011 | ሐምሌ 15
-
-
3. ኢየሱስ በዮሐንስ 5:16, 17 ላይ የተናገረው ሐሳብ ሰባተኛው ቀን በመጀመሪያው መቶ ዘመንም እንዳላበቃ የሚጠቁመው እንዴት ነው?
3 ሰባተኛው ቀን በመጀመሪያው መቶ ዘመንም ቢሆን አላበቃም ብለን እንድንደመድም የሚያደርጉን ሁለት ማስረጃዎች አሉ። በመጀመሪያ ኢየሱስ በሰንበት ቀን የታመሙ ሰዎችን መፈወሱ፣ ሥራ ከመሥራት ተለይቶ እንደማይታይ በማሰብ ተቃዋሚዎቹ ሲነቅፉት የሰጣቸውን መልስ እንመልከት። “አባቴ እስካሁን እየሠራ ነው፤ እኔም መሥራቴን እቀጥላለሁ” ብሏቸዋል። (ዮሐ. 5:16, 17) ኢየሱስ ምን ማለቱ ነበር? ተቃዋሚዎቹ ኢየሱስን በሰንበት ቀን ሠርተሃል ብለው ከሰውታል። ስለዚህ “አባቴ እስካሁን እየሠራ ነው” ሲል ለክሱ ምላሽ መስጠቱ ነበር። በሌላ አባባል ኢየሱስ እንዲህ ማለቱ ነበር፦ ‘እኔና አባቴ የምንሠራው አንድ ዓይነት ሥራ ነው። አባቴ በሺዎች ለሚቆጠሩ ዓመታት በዘለቀው የሰንበት እረፍቱ እየሠራ ስለሆነ እኔም በሰንበት ቀንም እንኳ መሥራት እችላለሁ።’ በመሆኑም ኢየሱስ ከሰው ልጆችና ከምድር ጋር በተያያዘ፣ ታላቁ የአምላክ የሰንበት እረፍት ማለትም ሰባተኛው ቀን በእሱ ዘመንም እንዳላበቃ ጠቁሟል።a
-
-
የአምላክ እረፍት ምንድን ነው?መጠበቂያ ግንብ—2011 | ሐምሌ 15
-
-
5. ይሖዋ በሰባተኛው ቀን ምን የማድረግ ዓላማ ነበረው? ይህ ዓላማ ሙሉ በሙሉ የሚፈጸመው መቼ ነው?
5 የዚህን ጥያቄ መልስ ለማግኘት የሰባተኛው ቀን ዓላማ ምን እንደሆነ ማስታወስ ይኖርብናል። ዘፍጥረት 2:3 “እግዚአብሔር ሰባተኛውን ቀን ባረከው፤ ቀደሰውም” ይላል። ይሖዋ ይህን ቀን ‘የቀደሰው’ ወይም የለየው ዓላማውን ከዳር ለማድረስ ነው። የይሖዋ ዓላማ፣ ምድር ታዛዥ በሆኑ ወንዶችና ሴቶች እንድትሞላ እንዲሁም እነዚህ ሰዎች ምድርንም ሆነ በውስጧ ያሉትን ሕያዋን ፍጥረታት እንዲንከባከቡ ነው። (ዘፍ. 1:28) ይሖዋ አምላክና “የሰንበት ጌታ” የተባለው ኢየሱስ ክርስቶስ ‘እስካሁን እየሠሩ’ ያሉት ይህን ዓላማ እውን ለማድረግ ነው። (ማቴ. 12:8) የአምላክ የእረፍት ቀን፣ በክርስቶስ የሺህ ዓመት ግዛት መጨረሻ ላይ ዓላማው ሙሉ በሙሉ እስከሚፈጸምበት ጊዜ ድረስ ይቀጥላል።
-
-
የአምላክ እረፍት ምንድን ነው?መጠበቂያ ግንብ—2011 | ሐምሌ 15
-
-
a ካህናቱና ሌዋውያኑ በሰንበት ቀን በቤተ መቅደስ ውስጥ የሚሠሩ ቢሆንም ‘እንደ በደል አይቆጠርባቸውም’ ነበር። ኢየሱስም የአምላክ ታላቅ መንፈሳዊ ቤተ መቅደስ ሊቀ ካህን እንደመሆኑ መጠን በሰንበት ዕለትም መንፈሳዊ ኃላፊነቱን መወጣት ይችል ነበር፤ እንዲህ ማድረጉ የሰንበትን ሕግ ጥሷል አያስብለውም።—ማቴ. 12:5, 6
-