-
“ማንም ሰው እንደዚህ ተናግሮ አያውቅም”ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
-
-
አንዳንዶች ኢየሱስ የተናገረውን ሲሰሙ “ይህ ሰው በእርግጥ ነቢዩ ነው” ይሉ ጀመር፤ ይህን ያሉት ሙሴ ከእሱ የሚበልጥ ነቢይ እንደሚነሳ የተነገረውን ትንቢት አስታውሰው መሆን አለበት። ሌሎችም “ይህ ክርስቶስ ነው” አሉ። አንዳንዶች ግን እንዲህ በማለት ተናገሩ፦ “ክርስቶስ የሚመጣው ከገሊላ ነው እንዴ? ቅዱስ መጽሐፉ ክርስቶስ ከዳዊት ዘርና ዳዊት ከኖረበት መንደር ከቤተልሔም እንደሚመጣ ይናገር የለም?”—ዮሐንስ 7:40-42
-
-
“ማንም ሰው እንደዚህ ተናግሮ አያውቅም”ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
-
-
ቅዱሳን መጻሕፍት ነቢይ ከገሊላ እንደሚነሳ በቀጥታ አይናገሩም። ያም ቢሆን የአምላክ ቃል ክርስቶስ የሚመጣው ከዚያ እንደሆነ ይገልጻል፤ “የአሕዛብ ገሊላ” “ታላቅ ብርሃን” እንደሚያይ ትንቢት ተነግሯል። (ኢሳይያስ 9:1, 2፤ ማቴዎስ 4:13-17) ከዚህም በላይ አስቀድሞ እንደተነገረው ኢየሱስ የተወለደው በቤተልሔም ነው፤ እንዲሁም የዳዊት ዘር ነው። ፈሪሳውያን ይህን ሳያውቁ አይቀሩም፤ ስለ ኢየሱስ በሕዝቡ መካከል የተሳሳተ አስተሳሰብ እንዲስፋፋ ያደረጉት እነሱ መሆን አለባቸው።
-