የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • በአምላክ ፊት ውድ ናችሁ!
    መጠበቂያ ግንብ—1995 | ሚያዝያ 1
    • 1. ኢየሱስ በእሱ ዘመን ለነበሩት ተራ ሰዎች የነበረው አመለካከት ፈሪሳውያን ለእነዚህ ሰዎች ከነበራቸው አመለካከት የሚለየው እንዴት ነው?

      ይህን ከፊቱ ማንበብ ይችሉ ነበር። ይህ ሰው ማለትም ኢየሱስ ከሃይማኖት መሪዎቻቸው ፈጽሞ የተለየ ነበር፤ በጣም ያስብላቸው ነበር። እነዚህ ሰዎች “እረኛ እንደ ሌላቸው በጎች ተጨንቀው ተጥለውም ነበርና” አዝኖላቸዋል። (ማቴዎስ 9:36) የሃይማኖት መሪዎቻቸው አፍቃሪና መሐሪ አምላክን የሚወክሉ አፍቃሪ እረኞች መሆን ይጠበቅባቸው ነበር። ተራውን ሕዝብ እንደ አልባሌ አድርገው በመመልከት ይንቁት ነበር፤ እንዲሁም ርጉም አድርገው ይመለከቱት ነበር!a (ዮሐንስ 7:47–49፤ ከሕዝቅኤል 34:4 ጋር አወዳድር።) ይህ የተዛባና ቅዱስ ጽሑፋዊ ድጋፍ የሌለው አመለካከት ይሖዋ ለሕዝቡ ካለው አመለካከት ጋር ፈጽሞ የማይገናኝ ነበር። ይሖዋ ሕዝቡን እስራኤልን “በዘላለም ፍቅር ወድጄሻለሁ” ብሏል።—ኤርምያስ 31:3

  • በአምላክ ፊት ውድ ናችሁ!
    መጠበቂያ ግንብ—1995 | ሚያዝያ 1
    • a እንዲያውም “አምሃሬትስ” ወይም “የምድር ሰዎች” በሚል የንቀት መጠሪያ በመጠቀም ድሀዎቹን ሰዎች አጣጥለዋቸው ነበር። አንድ ምሁር እንዳሉት ከሆነ ፈሪሳውያን አንድ ሰው ለእነዚህ ሰዎች ውድ የሆኑ ነገሮችን አምኖ ሊሰጣቸው፣ የምሥክርነት ቃላቸውን ሊያምን፣ በእንግድነት ሊያስተናግዳቸው፣ የእነርሱ እንግዳ ሆኖ ሊስተናገድ ወይም ሌላው ቀርቶ ከእነርሱ ሊገዛ አይገባውም ሲሉ አስተምረዋል። ሃይማኖታዊ መሪዎቹ አንድ ሰው ሴት ልጁን ከእነዚህ ሰዎች ለአንዱ መዳር ማለት ሁለት እጆቿን ጠፍሮ ለአውሬ አሳልፎ መስጠት ማለት ነው ብለው ይናገሩ ነበር።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ