-
‘ጊዜው ገና አልደረሰም’መጠበቂያ ግንብ—2000 | መስከረም 15
-
-
17. (ሀ) ኢየሱስ በፍርግያ እየሰበከ በነበረበት ወቅት ምን አስቸኳይ መልእክት ደረሰው? (ለ) ኢየሱስ እርምጃ መውሰድ ያለበት በምን ዓላማ እንደሆነና ሁኔታዎች በየትኛው ጊዜ መፈጸም እንዳለባቸው እንደሚያውቅ የሚያሳየው ምንድን ነው?
17 ይህ አስቸኳይ መልእክት በይሁዳ ቢታንያ ከሚኖሩት የአልዓዛር እህቶች ከማርታና ከማርያም የመጣ ነው። መልእክተኛው “ጌታ ሆይ፣ እነሆ፣ የምትወደው ታሞአል” ብሎ ነገረው። ኢየሱስ “ይህ እመም የእግዚአብሔር ልጅ በእርሱ ይከብር ዘንድ ስለ እግዚአብሔር ክብር ነው እንጂ ለሞት አይደለም” ሲል መለሰለት። ኢየሱስ ይህ ዓላማ ግቡን እንዲመታ ለማድረግ ሆነ ብሎ እዚያው ባለበት ለሁለት ቀናት ቆየ። ከዚያም ለደቀ መዛሙርቱ “ወደ ይሁዳ ደግሞ እንሂድ” አላቸው። ደቀ መዛሙርቱ በጥርጣሬ ስሜት “መምህር ሆይ፣ አይሁድ ከጥቂት ጊዜ በፊት ሊወግሩህ ይፈልጉ ነበር፣ ደግሞም ወደዚያ ትሄዳለህን?” አሉት። ሆኖም ኢየሱስ የቀረው ‘በቀን የሚመላለስበት ጊዜ’ ማለትም አምላክ ለምድራዊ አገልግሎቱ የመደበለት ጊዜ አጭር መሆኑን ተገንዝቧል። ማድረግ ያለበትንና ለምን ማድረግ እንዳለበት በሚገባ ያውቃል።—ዮሐንስ 11:1-10
-
-
‘ጊዜው ገና አልደረሰም’መጠበቂያ ግንብ—2000 | መስከረም 15
-
-
21. በተአምር የተፈጸመው የአልዓዛር ትንሣኤ ለምን ነገር መቅድም ነው?
21 በመሆኑም ኢየሱስ ወደ ቢታንያ ዘግይቶ በመምጣት የሰውን ሁሉ ትኩረት የሳበ ተአምር መፈጸም ችሏል። ኢየሱስ ከአምላክ ባገኘው ኃይል ለአራት ቀናት ሞቶ የነበረን ሰው አስነሳ። ሌላው ቀርቶ የታወቀው የሳንሄድሪን ሸንጎ እንኳ ሁኔታውን ለመቀበልና ተአምር በሠራው ሰው ላይ የሞት ፍርድ ለማስተላለፍ ተገድዷል! በመሆኑም ይህ ተአምር ‘ጊዜው ገና ያልደረሰበት’ ወቅት አልፎ ‘ሰዓቱ ወደደረሰበት’ ጊዜ ለተሸጋገረበት በኢየሱስ አገልግሎት ወሳኝ ለሆነ ለውጥ ዋዜማ ሆኖ አገልግሏል።
-