የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ትኩረታችሁ ሳይከፋፈል ይሖዋን አገልግሉ
    መጠበቂያ ግንብ—2015 | ጥቅምት 15
    • 1, 2. ኢየሱስ ማርታን ይወዳት የነበረው ለምንድን ነው? ሆኖም ፍጹም ሰው እንዳልሆነች የሚያሳየው ምንድን ነው?

      በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለተጠቀሰችው ስለ ማርታ ስታስብ ወደ አእምሮህ የሚመጣው ምንድን ነው? ኢየሱስ እንደሚወዳት በስም የተጠቀሰችው ብቸኛዋ ሴት እሷ ናት፤ እርግጥ ኢየሱስ አምላክን ለሚታዘዙ ለሌሎች ሴቶችም ከራስ ወዳድነት ነፃ የሆነ ፍቅር ነበረው፤ ለምሳሌ ሥጋዊ እናቱን ማርያምን እንዲሁም የማርታን እህት ማርያምን ይወድዳቸው ነበር። (ዮሐ. 11:5፤ 19:25-27) ታዲያ ማርታ በወንጌል ዘገባው ውስጥ በዚህ መንገድ የተገለጸችው ለምንድን ነው?

  • ትኩረታችሁ ሳይከፋፈል ይሖዋን አገልግሉ
    መጠበቂያ ግንብ—2015 | ጥቅምት 15
    • 4 ይሁን እንጂ ማርታ፣ አቅሟ በሚፈቅደው መጠን ኢየሱስን ለማስደሰት ለየት ያለ ምግብ በማዘጋጀትና ሌሎች ሥራዎችን በማከናወን ተጠምዳ ነበር። ይህ ሁሉ ሥራ ግን አላስፈላጊ ጭንቀት ስለፈጠረባት የማርያም ሁኔታ አበሳጫት። ኢየሱስ፣ ማርታ ብዙ ነገር ለማከናወን እየጣረች እንደሆነ ስላስተዋለ በደግነት “ማርታ፣ ማርታ፣ ስለ ብዙ ነገር ትጨነቂያለሽ፤ ደግሞም ትጠበቢያለሽ” አላት። አንድ ዓይነት ምግብ ብቻ በቂ እንደሆነ ሐሳብ ሰጣት። ከዚያም ኢየሱስ ትኩረቱን ወደ ማርያም ዞር በማድረግ “ማርያም በበኩሏ ጥሩ የሆነውን ድርሻ መርጣለች፤ ይህም ከእሷ አይወሰድም” በማለት ድርጊቷ እንደ ቸልተኝነት ሊታይ እንደማይገባ ተናገረ። ማርያም በዚህ ልዩ ወቅት የተመገበችውን ምግብ ብዙም ሳይቆይ ትረሳው ይሆናል፤ ይሁንና ትኩረቷ ሳይከፋፈል ኢየሱስን በማዳመጧ የተቸራትን ምስጋናም ሆነ ያገኘችውን ግሩም መንፈሳዊ ምግብ መቼም አትረሳውም። ሐዋርያው ዮሐንስ ከ60 ከሚበልጡ ዓመታት በኋላ “ኢየሱስ ማርታንና እህቷን . . . ይወዳቸው” እንደነበር ጽፏል። (ዮሐ. 11:5) በመንፈስ መሪነት የተጻፈው ይህ ሐሳብ ማርታ፣ ኢየሱስ የሰጣትን ፍቅራዊ እርማት እንደተቀበለችና በቀሪው ሕይወቷ ይሖዋን በታማኝነት ለማገልገል ጥረት እንዳደረገች በግልጽ ያሳያል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ