የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የሞቱ ሰዎች በምን ዓይነት ሁኔታ ላይ ይገኛሉ?
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
    • 3. የሞቱ ሰዎች የሚገኙበትን ሁኔታ በተመለከተ እውነታው ምንድን ነው?

      የሞቱ ሰዎች የሚገኙበትን ሁኔታ በተመለከተ በዓለም ዙሪያ የተለያየ አመለካከት አለ። መቼም እነዚህ ሁሉ አመለካከቶች እውነት ሊሆኑ እንደማይችሉ የታወቀ ነው።

      • የሞቱ ሰዎች የሚገኙበትን ሁኔታ በተመለከተ በአካባቢህ ያለው አመለካከት ምንድን ነው?

      መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚያስተምር ለማወቅ ቪዲዮውን ተመልከቱ።

      ቪዲዮ፦ ስንሞት ምን እንሆናለን?—ተቀንጭቦ የተወሰደ (1:19)

      ‘ስንሞት ምን እንሆናለን?—ተቀንጭቦ የተወሰደ’ ከተባለው ቪዲይ ላይ የተወሰደ ትዕይንት፦ 1. ሆስፒታል አልጋ ላይ ያለ የአንድ ሰው ሬሳ 2. አንድ ሰው በባቡር ሲጓዝ እንቅልፍ ወስዶት። ከግራውና ከቀኙ ሁለት ሰዎች አሉ

      መክብብ 3:20⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

      • በዚህ ጥቅስ መሠረት ሰው ከሞተ በኋላ ምን ይሆናል?

      • ሰው ሲሞት በሕይወት መኖሯን የምትቀጥል ነገር አለች?

      መጽሐፍ ቅዱስ የኢየሱስ የቅርብ ወዳጅ ስለነበረው ስለ አልዓዛር ሞት ይናገራል። ዮሐንስ 11:11-14⁠ን አንብቡ፤ ጥቅሱ ሲነበብ ኢየሱስ አልዓዛር የሚገኝበትን ሁኔታ የገለጸው እንዴት እንደሆነ ለማስተዋል ሞክር። ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

      • ኢየሱስ ሞትን ከምን ጋር አመሳስሎታል?

      • ይህ ንጽጽር የሞቱ ሰዎች ስለሚገኙበት ሁኔታ ምን ያስተምረናል?

      • መጽሐፍ ቅዱስ ሞትን በተመለከተ ስለሚያስተምረው ትምህርት ምን ይሰማሃል?

  • በሞት የተለዩህ የምትወዳቸው ሰዎች ዳግመኛ በሕይወት ይኖራሉ!
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
    • ኢየሱስ አልዓዛርን ከሞት ሲያስነሳው ሌሎች በአግራሞት ሲመለከቱ

      4. ኢየሱስ የሞቱ ሰዎችን ማስነሳት እንደሚችል አሳይቷል

      ኢየሱስ ለወዳጁ ለአልዓዛር ያደረገውን ነገር በስፋት እንመልከት። ዮሐንስ 11:14, 38-44⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

      • አልዓዛር በእርግጥ ሞቶ እንደነበር እንዴት እናውቃለን?—ቁጥር 39⁠ን ተመልከት።

      • አልዓዛር ወደ ሰማይ ሄዶ ቢሆን ኖሮ ኢየሱስ መልሶ ወደ ምድር እንዲመጣ የሚያደርገው ይመስልሃል?

      ቪዲዮውን ተመልከቱ።

      ቪዲዮ፦ ኢየሱስ አልዓዛርን ከሞት አስነስቶታል (1:16)

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ