የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የማያምኑ ዘመዶቻችንን ልብ መንካት
    መጠበቂያ ግንብ—2014 | መጋቢት 15
    • በአንደኛው መቶ ዘመን ይኖር የነበረው እንድርያስ፣ ኢየሱስ መሲሕ እንደሆነ ካስተዋሉት የመጀመሪያ ሰዎች መካከል አንዱ ነው። ታዲያ ያወቀውን ነገር ወዲያውኑ የተናገረው ለማን ነው? “እንድርያስ በመጀመሪያ የራሱን ወንድም ስምዖንን አገኘውና ‘መሲሑን (ትርጉሙ ክርስቶስ ማለት ነው) አገኘነው’ አለው።” እንድርያስ ጴጥሮስን ወደ ኢየሱስ የወሰደው ሲሆን ይህን በማድረጉም ጴጥሮስ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር እንዲሆን አጋጣሚ ከፍቶለታል።—ዮሐ. 1:35-42

  • የማያምኑ ዘመዶቻችንን ልብ መንካት
    መጠበቂያ ግንብ—2014 | መጋቢት 15
    • እንድርያስና ቆርኔሌዎስ፣ ለዘመዶቻቸው ካደረጉት ነገር ምን ትምህርት እናገኛለን?

      እንድርያስም ሆነ ቆርኔሌዎስ ዘመዶቻቸው እውነትን እንዲሰሙ ለማድረግ አንዳንድ እርምጃዎችን ወስደዋል። እንድርያስ፣ ጴጥሮስን ወስዶ ከኢየሱስ ጋር አስተዋውቆታል፤ ቆርኔሌዎስም ዘመዶቹ የጴጥሮስን ንግግር እንዲያዳምጡ ሁኔታዎችን አመቻችቷል። ይሁንና እንድርያስም ሆነ ቆርኔሌዎስ በዘመዶቻቸው ላይ ጫና አላሳደሩባቸውም፤ ወይም ደግሞ ብልጠት ተጠቅመው የክርስቶስ ተከታዮች እንዲሆኑ ለማድረግ አልሞከሩም። ከዚህ ምን ትምህርት ማግኘት እንችላለን? እኛም እንደ እነሱ ብናደርግ የተሻለ ውጤት እናገኛለን። ለዘመዶቻችን አንዳንድ ሐሳቦችን ልናካፍላቸው እንዲሁም የመጽሐፍ ቅዱስን እውነቶች እንዲያውቁና ከእምነት ባልንጀሮቻችን ጋር እንዲተዋወቁ አጋጣሚ ልናመቻችላቸው እንችላለን። ያም ቢሆን የራሳቸውን ምርጫ የማድረግ መብታቸውን ማክበርና አላስፈላጊ ጫና ከማድረግ መቆጠብ ይኖርብናል። ዩርገን እና ፔትራ የተባሉ በጀርመን የሚኖሩ ባልና ሚስት ተሞክሮ፣ ዘመዶቻችንን እንዴት መርዳት እንደምንችል የሚያሳይ ጥሩ ምሳሌ ነው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ