-
ይሖዋ ሥቃያችንን ይረዳልናልመጠበቂያ ግንብ—2008 | ግንቦት 1
-
-
ኢየሱስ፣ ወዳጁ አልዓዛር ያለ ዕድሜው በሞት በተቀጨ ጊዜ አልዓዛር ወደሚኖርበት መንደር ሄደ። የአልዓዛር እህቶች ማርያምና ማርታ በሐዘን ተደቁሰው እንደሚሆን የታወቀ ነው። ኢየሱስ ይህን ቤተሰብ በጣም ይወደው ነበር። (ዮሐንስ 11:5) ታዲያ ምን ያደርግ ይሆን? ዘገባው እንዲህ ይላል:- “ኢየሱስም [ማርያም] ስታለቅስ፣ ተከትለዋትም የመጡት አይሁድም ሲያለቅሱ ባየ ጊዜ መንፈሱ በኀዘን ታውኮ፣ ‘የት ነው ያኖራችሁት?’ ሲል ጠየቀ። እነርሱም፣ ‘ጌታ ሆይ፤ መጥተህ እይ’ አሉት። ኢየሱስም እንባውን አፈሰሰ።” (ዮሐንስ 11:33-35) ኢየሱስ ያለቀሰው ለምን ነበር? ወዳጁ አልዓዛር እንደሞተ እሙን ነው፤ ቢሆንም ኢየሱስ ከጥቂት ጊዜ በኋላ አልዓዛርን ከሞት ያስነሳዋል። (ዮሐንስ 11:41-44) ታዲያ ኢየሱስ እንዲያዝን ያደረገው ሌላ ነገር ይኖር ይሆን?
እስቲ ከላይ የተጠቀሰውን ሐሳብ በድጋሚ ተመልከት። ኢየሱስ፣ ማርያምና አብረዋት የነበሩት ሰዎች ሲያለቅሱ ሲመለከት ‘መንፈሱ በኀዘን እንደታወከ’ ልብ በል። ይህን ሐሳብ ለመግለጽ የገባው የግሪክኛ አባባል ጥልቅ ስሜትን ያመለክታል።a ኢየሱስ ያየው ነገር በጥልቅ ነክቶታል፤ ዓይኖቹ በእንባ ግጥም ማለታቸው ለዚህ ማስረጃ ነው። በግልጽ ማየት እንደሚቻለው ኢየሱስ በሰዎች ላይ ሥቃይ ሲደርስ ያዝናል። አንተስ የምትወደው ሰው ሲያለቅስ ስታይ አልቅሰህ ታውቃለህ?—ሮሜ 12:15
-
-
ይሖዋ ሥቃያችንን ይረዳልናልመጠበቂያ ግንብ—2008 | ግንቦት 1
-
-
a “እንባውን አፈሰሰ” ተብሎ የተተረጎመው የግሪክኛ ቃል አብዛኛውን ጊዜ “ድምፅ ሳያሰሙ ማልቀስን” ያመለክታል፤ ማርያምና ሌሎቹ ሰዎች ያለቀሱበትን መንገድ ለመግለጽ የገባው ቃል ግን “ድምፅ አውጥቶ ወይም እዬዬ ብሎ ማልቀስን” ሊያመለክት ይችላል።
-