የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • jy ምዕ. 15 ገጽ 40-ገጽ 41 አን. 6
  • ኢየሱስ የፈጸመው የመጀመሪያ ተአምር

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ኢየሱስ የፈጸመው የመጀመሪያ ተአምር
  • ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የመጀመሪያው የኢየሱስ ተአምር
    እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው
  • በቃና የፈጸመው ሁለተኛ ተአምር
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • በቃና የፈጸመው ሁለተኛው ተአምር
    እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው
  • የአንባቢያን ጥያቄዎች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
ለተጨማሪ መረጃ
ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
jy ምዕ. 15 ገጽ 40-ገጽ 41 አን. 6
በቃና በአንድ ሠርግ ላይ ኢየሱስ አስተናጋጆቹ ጋኖቹን ውኃ እንዲሞሉ ሲያዛቸው

ምዕራፍ 15

ኢየሱስ የፈጸመው የመጀመሪያ ተአምር

ዮሐንስ 2:1-12

  • በቃና የተደረገ ሠርግ

  • ኢየሱስ ውኃውን ወደ ወይን ጠጅ ለወጠ

ናትናኤል ከኢየሱስ የመጀመሪያ ደቀ መዛሙርት አንዱ ከሆነ ሦስተኛ ቀኑ ነው። ኢየሱስ፣ ከመጀመሪያዎቹ ደቀ መዛሙርቱ መካከል ከአንዳንዶቹ ጋር በመሆን ወዳደጉበት አካባቢ ማለትም በስተ ሰሜን ወደምትገኘው የገሊላ አውራጃ እየተጓዘ ነው። የሚሄዱት ወደ ቃና ሲሆን ናትናኤል የመጣው ከዚህች ከተማ ነው። ቃና፣ ኢየሱስ ካደገባት ከናዝሬት በስተ ሰሜን ኮረብታ ላይ ትገኛለች። በዚህች ከተማ በአንድ የሠርግ ድግስ ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል።

የኢየሱስ እናትም ወደ ሠርጉ መጥታለች። ማርያም የሙሽሮቹ ቤተሰብ ወዳጅ በመሆኗ ወደ ሠርጉ የተጠሩትን ብዙ እንግዶች በማስተናገድ ረገድ ድርሻ የነበራት ይመስላል። በመሆኑም የጎደለ ነገር መኖሩን ልክ ስታስተውል “የወይን ጠጅ አልቆባቸዋል” ብላ ለኢየሱስ ነገረችው።—ዮሐንስ 2:3

ማርያም የወይን ጠጅ በማለቁ ኢየሱስ አንድ ነገር እንዲያደርግ መጠቆሟ ነበር። ኢየሱስ፣ በሐሳቧ አለመስማማቱን ለመግለጽ ፈሊጣዊ አነጋገር በመጠቀም “አንቺ ሴት፣ ይህ ጉዳይ እኔንና አንቺን ምን ይመለከተናል?” ሲል ጠየቃት። (ዮሐንስ 2:4) በአምላክ የተሾመ ንጉሥ እንደ መሆኑ መጠን እንቅስቃሴውን የሚመራው በሰማይ ያለው አባቱ እንጂ ቤተሰቡ ወይም ጓደኞቹ አይደሉም። ማርያምም በዚያ የሚያገለግሉትን ሰዎች “የሚላችሁን ነገር ሁሉ አድርጉ” በማለት ጉዳዩን ለልጅዋ ተወችው፤ በዚህ መንገድ ጥበብ አሳይታለች።—ዮሐንስ 2:5

በሠርጉ ቦታ፣ እያንዳንዳቸው ከ40 ሊትር በላይ ሊይዙ የሚችሉ ከድንጋይ የተሠሩ ስድስት ጋኖች ነበሩ። ኢየሱስ፣ የሚያስተናግዱትን ሰዎች “ጋኖቹን ውኃ ሙሏቸው” አላቸው። ከዚያም “አሁን ቀድታችሁ ለድግሱ አሳዳሪ ስጡት” ብሎ ነገራቸው።—ዮሐንስ 2:7, 8

የድግሱ አሳዳሪ ስለ ወይን ጠጁ ጥራት ሙሽራውን ሲያመሰግነው

አሳዳሪው በወይን ጠጁ ጣዕምና ጥራት በጣም ተደነቀ፤ ሆኖም የወይን ጠጁ ተአምራዊ በሆነ መንገድ እንደተገኘ አላወቀም። በመሆኑም ሙሽራውን ጠርቶ “ሰው ሁሉ በቅድሚያ ጥሩውን የወይን ጠጅ ያቀርብና ሰዎቹ ከሰከሩ በኋላ መናኛውን ያቀርባል። አንተ ግን ጥሩውን የወይን ጠጅ እስካሁን ድረስ አስቀምጠሃል” አለው።—ዮሐንስ 2:10

ኢየሱስ የፈጸመው የመጀመሪያው ተአምር ይህ ነው። አዳዲሶቹ ደቀ መዛሙርት ይህን ሲያዩ በእሱ ላይ ያላቸው እምነት ተጠናከረ። ከዚያ በኋላ ኢየሱስ ከእናቱና ከወንድሞቹ ጋር ሆኖ ከገሊላ ባሕር በስተ ሰሜን ምዕራብ ወደምትገኘው ቅፍርናሆም የተባለች ከተማ ተጓዘ።

  • ከኢየሱስ አገልግሎት አንጻር የቃናው ሠርግ የተከናወነው መቼ ነው?

  • ኢየሱስ፣ እናቱ የወይን ጠጅ ማለቁን ስትነግረው ምን ምላሽ ሰጠ?

  • ኢየሱስ ምን ተአምር ፈጸመ? ይህስ ምን ውጤት አስገኘ?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ