የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ይሖዋ “በጽናት ፍሬ የሚያፈሩ” ሰዎችን ይወዳል
    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2018 | ግንቦት
    • 7. (ሀ) “አትክልተኛው፣” “የወይኑ ተክል” እንዲሁም “ቅርንጫፎቹ” እነማንን ያመለክታሉ? (ለ) የየትኛውን ጥያቄ መልስ ማግኘት ያስፈልገናል?

      7 ዮሐንስ 15:1-5, 8⁠ን አንብብ። ኢየሱስ ሐዋርያቱን “ብዙ ፍሬ ብታፈሩና ደቀ መዛሙርቴ መሆናችሁን ብታሳዩ በዚህ አባቴ ይከበራል” እንዳላቸው ልብ እንበል። በምሳሌው ላይ “አትክልተኛው” ይሖዋን፣ “እውነተኛው የወይን ተክል” ኢየሱስን እንዲሁም “ቅርንጫፎቹ”b ደቀ መዛሙርቱን እንደሚያመለክቱ ተገልጿል። ታዲያ የክርስቶስ ተከታዮች ማፍራት ያለባቸው ፍሬ ምንድን ነው? ኢየሱስ ይህ ፍሬ ምን እንደሆነ በቀጥታ አልተናገረም፤ ሆኖም የፍሬውን ምንነት ለማወቅ የሚረዳ ጠቃሚ ፍንጭ ሰጥቶናል።

      8. (ሀ) በምሳሌው ላይ የተጠቀሰው ፍሬ አዳዲስ ደቀ መዛሙርትን ሊያመለክት አይችልም የምንለው ለምንድን ነው? (ለ) ይሖዋ ከአገልጋዮቹ የሚጠብቀውን ነገር በተመለከተ እርግጠኞች መሆን የምንችልበት ሐቅ የትኛው ነው?

      8 ኢየሱስ “በእኔ ላይ ያለውን፣ ፍሬ የማያፈራውን ቅርንጫፍ ሁሉ [አባቴ] ቆርጦ ይጥለዋል” ብሏል። በሌላ አባባል ይሖዋ እንደ አገልጋዮቹ አድርጎ የሚመለከተን ፍሬ የምናፈራ ከሆነ ብቻ ነው። (ማቴ. 13:23፤ 21:43) ስለሆነም በዚህ ምሳሌ ላይ እያንዳንዱ ክርስቲያን ማፍራት እንዳለበት የተጠቀሰው ፍሬ፣ አዳዲስ ደቀ መዛሙርት ማስገኘትን የሚያመለክት ሊሆን አይችልም። (ማቴ. 28:19) ይህ ባይሆን ኖሮ አብዛኞቹ ሰዎች ምሥራቹን በማይቀበሉበት ክልል ውስጥ የሚያገለግሉ ታማኝ ክርስቲያኖች፣ አዳዲስ ደቀ መዛሙርት ማስገኘት ባለመቻላቸው ምክንያት በኢየሱስ ምሳሌ ላይ እንደተጠቀሱት ፍሬ የማያፈሩ ቅርንጫፎች ይቆጠሩ ነበር። ይሁንና ይህ ጨርሶ ሊሆን የማይችል ነገር ነው! ለምን? ምክንያቱም ሰዎች የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት እንዲሆኑ ማስገደድ አንችልም። ይህ ከእኛ ቁጥጥር ውጭ የሆነ ነገር ነው፤ አፍቃሪ የሆነው አምላካችን ይሖዋ ደግሞ ከአቅማችን በላይ የሆነውን ነገር ባለማድረጋችን ምክንያት አገልጋዮቹ ለመሆን ብቁ እንዳልሆንን አድርጎ ይመለከተናል ብሎ ማሰብ የማይመስል ነገር ነው። ይሖዋ ምንጊዜም ቢሆን ማድረግ የማንችለውን ነገር አይጠብቅብንም።—ዘዳ. 30:11-14

      9. (ሀ) ፍሬ ማፍራት የምንችለው የትኛውን ሥራ በማከናወን ነው? (ለ) የትኛውን ምሳሌ እንመለከታለን? ለምንስ?

      9 ለመሆኑ ልናፈራው የሚገባው ፍሬ ምንድን ነው? ፍሬው፣ ሁላችንም ልናከናውን የምንችለውን ሥራ የሚያመለክት መሆን አለበት። ታዲያ ‘ፍሬ እንደማፍራት’ ሊቆጠር የሚችለው ሥራ የትኛው ነው? የአምላክን መንግሥት ምሥራች መስበክ ነው።c (ማቴ. 24:14) ኢየሱስ ስለ አንድ ዘሪ የተናገረው ምሳሌ ይህን ያረጋግጣል። እስቲ ይህን ምሳሌ ደግሞ እንመልከት።

  • ይሖዋ “በጽናት ፍሬ የሚያፈሩ” ሰዎችን ይወዳል
    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2018 | ግንቦት
    • b በዚህ ምሳሌ ላይ የተጠቀሱት ቅርንጫፎች የሚያመለክቱት ወደ ሰማይ የመሄድ ተስፋ ያላቸውን ሰዎች ቢሆንም ከምሳሌው ሁሉም የአምላክ አገልጋዮች ትምህርት ማግኘት ይችላሉ።

      c ‘ፍሬ ማፍራት’ የሚለው አገላለጽ “የመንፈስ ፍሬ” ማፍራትንም ያመለክታል፤ ይሁንና በዚህና በሚቀጥለው ርዕስ ላይ ትኩረት የምናደርገው ‘የከንፈራችንን ፍሬ’ በማፍራት ወይም የስብከቱን ሥራ በማከናወን ላይ ነው።—ገላ. 5:22, 23፤ ዕብ. 13:15

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ