የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “ይህችን የወይን ተክል ተንከባከባት”!
    መጠበቂያ ግንብ—2006 | ሰኔ 15
    • ይሖዋ ሥጋዊ እስራኤላውያንን ከወይን ተክል ጋር እንዳመሳሰላቸው ሁሉ ኢየሱስም ተመሳሳይ የሆነ ምሳሌ ተጠቅሞል። ኢየሱስ በሕይወት ባሳለፈው የመጨረሻ ምሽት ላይ ለደቀ መዛሙርቱ “እውነተኛው የወይን ተክል እኔ ነኝ፤ አትክልተኛውም አባቴ ነው” በማለት ነግሯቸዋል። (ዮሐንስ 15:1) ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ከወይን ቅርንጫፎች ጋር አመሳስሏቸዋል። የአንድ የወይን ተክል ቅርንጫፍ ጥንካሬ የተመካው በግንዱ ላይ እንደሆነ ሁሉ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርትም ከእርሱ ጋር ያላቸውን አንድነት ጠብቀው መኖር ነበረባቸው። ኢየሱስ “ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉም” ሲል ነግሯቸዋል። (ዮሐንስ 15:5) ገበሬዎች ወይን የሚተክሉት ለፍሬው ሲሉ ነው፤ ይሖዋም ቢሆን ሕዝቦቹን መንፈሳዊ ፍሬ እንዲያፈሩ ይጠብቅባቸዋል። ይህም የወይኑ አትክልተኛ ለሆነው አምላክ እርካታና ክብር ያስገኝለታል።—ዮሐንስ 15:8

  • “ይህችን የወይን ተክል ተንከባከባት”!
    መጠበቂያ ግንብ—2006 | ሰኔ 15
    • ‘ብዙ ፍሬ ማፍራታችሁን ቀጥሉ’

      የምሳሌያዊው ‘እውነተኛ የወይን ተክል’ ቅርንጫፎች ቅቡዓን ክርስቲያኖችን ያመለክታሉ፤ ሆኖም ‘ሌሎች በጎችም’ ቢሆኑ ፍሬያማ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት መሆናቸውን ማስመስከር ይጠበቅባቸዋል። (ዮሐንስ 10:16) እነርሱም “ብዙ ፍሬ” በማፍራት በሰማይ የሚኖረውን አባታቸውን ማስከበር ይችላሉ። (ዮሐንስ 15:5, 8) ኢየሱስ እውነተኛውን የወይን ተክል አስመልክቶ የተናገረው ምሳሌ መዳናችን የተመካው ከክርስቶስ ጋር ያለንን አንድነት አጽንተን በመያዛችንና መልካም የሆኑ መንፈሳዊ ፍሬዎች በማፍራታችን ላይ መሆኑን እንድንረዳ ያስችለናል። ኢየሱስ “እኔ የአባቴን ትእዛዝ ጠብቄ በፍቅሩ እንደምኖር፣ እናንተም ትእዛዜን ብትጠብቁ በፍቅሬ ትኖራላችሁ” ብሏል።—ዮሐንስ 15:10

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ