የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ‘መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ የሚገባው ማን ነው?’
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • 7. ኢየሱስ ጥቅልሉን በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠው እጅ ለመውሰድ ብቁ እንዲሆን ያስቻለው ምንድን ነው?

      7 ኢየሱስ ፍጹም ሰው በነበረበት ጊዜ ፍጹም አቋሙን ጠብቆ ይሖዋን በታማኝነት አገልግሎአል። በጣም ከባድ በሆነ ፈተናም ጸንቶአል። ሰይጣን ላቀረበው ግድድር የተሟላ ምላሽ ሰጥቶአል። (ምሳሌ 27:11) በዚህም ምክንያት መስዋዕታዊ ሞት ከመሞቱ በፊት በነበረው ምሽት እንደተናገረው “እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ” ለማለት ችሎአል። (ዮሐንስ 16:33) በዚህም ምክንያት ይሖዋ ከሙታን ለተነሳው ኢየሱስ “ሥልጣን ሁሉ . . . በሰማይና በምድር” ሰጥቶታል። ከአምላክ አገልጋዮች መካከል ጥቅልሉን ለመቀበልና በጥቅልሉ ውስጥ የሚገኘውን መልእክት ለማሳወቅ ብቁ ሆኖ የተገኘው ኢየሱስ ብቻ ነው።—ማቴዎስ 28:18

  • ‘መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ የሚገባው ማን ነው?’
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • 11. ከፍተኛ ክብር የተቀዳጀውን ኢየሱስ ‘ታርዶ የነበረው በግ’ ብሎ መጥራት እርሱን ማዋረድ የማይሆነው ለምንድን ነው?

      11 ከፍተኛ ክብር የተጎናፀፈውን ኢየሱስ ‘በታረደ በግ’ መመሰል እርሱን ማዋረድ ወይም ማቃለል ይሆናልን? በፍጹም አይሆንም። ኢየሱስ እስከ ሞት ድረስ ታማኝነቱን ጠብቆ መኖሩ ለሰይጣን ትልቅ ሽንፈት ለይሖዋ ደግሞ ታላቅ ድል ነበር። ኢየሱስን በዚህ ዓይነት ምሳሌ ማቅረብ በሰይጣን ዓለም ላይ ያገኘውን ድል በግልጽ ከማሳየቱም በላይ ይሖዋና ኢየሱስ ለሰው ልጆች ያላቸውን ጥልቅ ፍቅር ያስታውሳል። (ዮሐንስ 3:16፤ 15:13፤ ከ⁠ቆላስይስ 2:15 ጋር አወዳድር።) ስለዚህ ኢየሱስ የተስፋው ዘር እንደሆነና የመጽሐፉን ጥቅልል ለመክፈት ሙሉ ብቃት እንዳለው ተጠቅሶአል።—ዘፍጥረት 3:15

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ