የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “አዲሲቱ ዓለም ትርጉም”​—ምሁራን እውነተኛ ሆኖ አግኝተውታል
    መጠበቂያ ግንብ—1991 | መጋቢት 1
    • በዮሐንስ 1:1 ላይ አዲሲቱ ዓለም ትርጉም እንዲህ ይነበባል፦ “ቃልም አምላክ ነበረ።” (እዚህ ላይ አምላክ ለማለት የገባው የእንግሊዝኛው ቃል ‘a god’ ነው።) በብዙ ሌሎች ትርጉሞች ግን ይህ ጥቅስ የተተረጐመው “The Word was God” (“ቃልም እግዚአብሔር ነበር”) ተብሎ ነው። ይህም የስላሴን ትምህርት ለመደገፍ ይሠራበታል። እንግዲያውስ የስላሴ ደጋፊዎች የአዲሲቱ ዓለም ትርጉምን ቢጠሉት አያስደንቅም። ይሁን እንጂ ዮሐንስ 1:1 ኢየሱስ ሁሉን ቻይ አምላክ አለመሆኑን ለማሳየት ተብሎ በሐሰት ተጣሞ የተተረጐመ አይደለም። የመጀመሪያውን ቋንቋ በትክክል ለመተርጎም የሚጥረው አዓት ገና ከመውጣቱ በፊትም የይሖዋ ምሥክሮች ‘god’ የሚለውን ቃል በትልቁ መጻፍ ትክክል አይደለም ብለው ሲከራከሩ ነበር። አምስት የጀርመንኛ መጽሐፍ ቅዱስ ተርጓሚዎችም በተመሳሳይ በዚያ ጥቅስ ላይ ‘a god’ የሚለውን አባባል ተጠቅመዋል።b ቢያንስ 13 ሌሎች ትርጉሞች ‘መለኰት መሳይ’ ወይም ‘አምላክ መሳይ’ በመሳሰሉት አገላለጾች ተጠቅመዋል። እነዚህ አተረጓጐሞች ከሌሎቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ጋር ይስማማሉ። በሰማይ ሳለ ኢየሱስ ‘a god’ ነው ለማለት ይቻላል ምክንያቱም መለኰታዊ ነው። ይሁን እንጂ ይሖዋና ኢየሱስ አንድ ሕላዌ ወይም አካል ወይም አንድ አምላክ አይደሉም።​—ዮሐንስ 14:28፤ 20:17

  • “አዲሲቱ ዓለም ትርጉም”​—ምሁራን እውነተኛ ሆኖ አግኝተውታል
    መጠበቂያ ግንብ—1991 | መጋቢት 1
    • b ጃርገን ቤከር፣ ጀረምያስ ፈልቢንገር፣ ኦስካር ሆልዝማን፣ ፍሬዴክ ሪትልሜየርና ሲግፍሬድ እስኩልዝ። ኤሚል ቦክ “መለኰታዊ አካል” ብሎታል። እንዲሁም የዛሬው የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም (Today’s English Version) አዲሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም (The New English Bible) የሞፋት፣ የጉድስፒድ የእንግሊዝኛ ትርጉሞችን ተመልከቱ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ