-
አምላክ የሚቀበለው አምልኮለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
1. አምልኳችን በምን ላይ የተመሠረተ ሊሆን ይገባል?
አምልኳችን በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ ሊሆን ይገባል። ኢየሱስ ወደ አምላክ ሲጸልይ “ቃልህ እውነት ነው” በማለት ተናግሯል። (ዮሐንስ 17:17) አንዳንድ ሃይማኖቶች በአምላክ መንፈስ መሪነት በተጻፈው ቃሉ ማለትም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለውን እውነት ችላ ይላሉ። ይህን እውነት በሰዎች ትምህርትና ወግ ተክተውታል። ይሖዋ ግን ‘ትእዛዙን ገሸሽ በሚያደርጉ’ ሰዎች ደስ አይሰኝም። (ማርቆስ 7:9ን አንብብ።) በሌላ በኩል ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ ስንመራና በውስጡ የሚገኘውን ምክር ተግባራዊ ስናደርግ ልቡን ደስ እናሰኛለን።
-
-
የይሖዋ ምሥክሮች እውነተኛ ክርስቲያኖች ናቸው?ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
1. የይሖዋ ምሥክሮች የሚያምኑበት ነገር በምን ላይ የተመሠረተ ነው?
ኢየሱስ “[የአምላክ ቃል] እውነት ነው” ብሏል። (ዮሐንስ 17:17) ልክ እንደ ኢየሱስ ሁሉ የይሖዋ ምሥክሮችም የሚያምኑበት ነገር ምንጊዜም በአምላክ ቃል ላይ የተመሠረተ ነው። እስቲ የይሖዋ ምሥክሮች ያሳለፉትን ታሪክ ተመልከት። የይሖዋ ምሥክሮች ቀደም ሲል የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ተብለው ይጠሩ ነበር። በ19ኛው መቶ ዘመን መጨረሻ አካባቢ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎቹ የአምላክን ቃል በጥንቃቄ መመርመር የጀመሩ ሲሆን የሚያምኑበት ነገር ሙሉ በሙሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ እንዲሆን አድርገዋል። አብያተ ክርስቲያናት ከሚያስተምሩት ትምህርት የተለየ አቋም መያዝ በሚኖርባቸው ጊዜም እንኳ እንዲህ ከማድረግ ወደኋላ አላሉም። በኋላም እነዚህን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች ለሌሎች መናገር ጀመሩ።a
-