የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ከኒቆዲሞስ ተማሩ
    መጠበቂያ ግንብ—2002 | የካቲት 1
    • ኒቆዲሞስ፣ ኢየሱስ ምድራዊ አገልግሎቱን ከጀመረ ከስድስት ወር ገደማ በኋላ ‘ከአምላክ ዘንድ ተልኮ የመጣ መምህር መሆኑን’ ተገነዘበ። ኒቆዲሞስ፣ ኢየሱስ በ30 እዘአ በተከበረው የማለፍ በዓል ዕለት በኢየሩሳሌም ባደረጋቸው ተአምራት በጣም በመገረሙ በኢየሱስ እንደሚያምን ለመናገርና ስለዚህ መምህር ይበልጥ ለመማር በጨለማ ተደብቆ መጣ። በዚህ ጊዜ ኢየሱስ ወደ አምላክ መንግሥት ለመግባት ‘ዳግም መወለድ’ አስፈላጊ መሆኑን ስለሚገልጸው ጥልቅ እውነት ለኒቆዲሞስ ነገረው። ኢየሱስ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና” የሚሉትን ቃላት የተናገረው በዚህ ጊዜ ነበር።​—⁠ዮሐንስ 3:​1-16

      ኒቆዲሞስ እንዴት ያለ አስደናቂ ተስፋ ተዘርግቶለታል! የኢየሱስን ምድራዊ ሕይወት የተለያዩ ገጽታዎች በቀጥታ በመመልከት የኢየሱስ የቅርብ ወዳጅ መሆን ይችል ነበር። ኒቆዲሞስ የአይሁድ አለቃና በእስራኤል ውስጥ መምህር እንደመሆኑ መጠን ጥሩ የአምላክ ቃል እውቀት ነበረው። በተጨማሪም ኢየሱስ ከአምላክ ዘንድ የመጣ መምህር መሆኑን መለየት መቻሉ ግሩም ማስተዋል እንደነበረው የሚያሳይ ነው። ኒቆዲሞስ ለመንፈሳዊ ጉዳዮች ትኩረት የሚሰጥ ከመሆኑም በላይ ትሑት ሰው ነበር። የአይሁድ ከፍተኛው ፍርድ ቤት አባል የሆነ አንድ ሰው አንድን ተራ የአናጢ ልጅ ከአምላክ ዘንድ የተላከ ሰው አድርጎ መቀበል ምንኛ የሚከብድ ነው! እነዚህ ሁሉ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ከሚሆን ሰው የሚፈለጉ ባሕርያት ናቸው።

  • ከኒቆዲሞስ ተማሩ
    መጠበቂያ ግንብ—2002 | የካቲት 1
    • በመጀመሪያ ደረጃ፣ ዮሐንስ ይህ የአይሁድ አለቃ “በሌሊት ወደ ኢየሱስ” መምጣቱን ጠቅሷል። (ዮሐንስ 3:​2) አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁር “ኒቆዲሞስ በሌሊት የመጣው ፈርቶ ሳይሆን ከኢየሱስ ጋር ውይይት በሚያደርግበት ጊዜ ሕዝቡ ጣልቃ እንዳይገባበት አስቦ ነው” የሚል አስተያየት ሰንዝረዋል። ይሁን እንጂ ዮሐንስ ኒቆዲሞስን “አስቀድሞ በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ የነበረ” ሲል ገልጾታል። ይህን ያለው የአርማቲያሱ ዮሴፍን በተመለከተ “አይሁድን ስለ ፈራ በስውር የኢየሱስ ደቀ መዝሙር የነበረ” በማለት ከሰጠው መግለጫ ጋር አያይዞ መሆኑ ትኩረት የሚስብ ነው። (ዮሐንስ 19:​38, 39) ስለሆነም በዘመኑ የነበሩ ሌሎች ሰዎች ስለ ኢየሱስ መናገር ይፈሩ እንደነበረ ሁሉ ኒቆዲሞስም በጨለማ ተደብቆ ወደ ኢየሱስ የመጣው “አይሁድን ስለ ፈራ” እንደሚሆን መገመት አያዳግትም።​—⁠ዮሐንስ 7:​13

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ