-
ለጥንቱ የምህንድስና ጥበብ ቅርስ የሆኑት የሮማውያን መንገዶችመጠበቂያ ግንብ—2006 | ጥቅምት 15
-
-
አፒያን ዌይ ከተሠራ ከ900 ዓመታት በኋላ ባይዛንታይናዊው ታሪክ ጸሐፊ ፕሮኮፒየስ ይህን መንገድ “ድንቅ” በማለት ጠርቶታል። ፕሮኮፒየስ በመንገዱ ላይ የነበሩትን የድንጋይ ንጣፎች አስመልክቶ እንዲህ ብሏል:- “ረጅም ዕድሜ ያሳለፉ እንዲሁም ይህ ነው የማይባል ብዛት ያላቸው ሰረገላዎችና ሌሎች ተሽከርካሪዎች በየቀኑ ሲመላለሱባቸው የቆዩ ቢሆኑም አልተፈነቃቀሉም እንዲሁም አባጣ ጎባጣ አልሆኑም።”
-
-
ለጥንቱ የምህንድስና ጥበብ ቅርስ የሆኑት የሮማውያን መንገዶችመጠበቂያ ግንብ—2006 | ጥቅምት 15
-
-
የሆነ ሆኖ ክርስቲያን ወንጌላውያን በርካታ የረጅም ርቀት ጉዞዎችን ለማድረግ ማቀድና ይህንንም ከግብ ማድረስ ችለዋል። ሐዋርያው ጳውሎስ በዘመኑ የነበሩ ብዙ ሰዎች ያደርጉት እንደነበረው ሁሉ ወደ ምሥራቅ ሲሄድ ብዙውን ጊዜ ነፋስ ስለሚኖር ለመጓዝ የሚመርጠው በመርከብ ነበር። (የሐዋርያት ሥራ 14:25, 26፤ 20:3፤ 21:1-3) በሜድትራንያን ባሕር ላይ በበጋ ወራት ከምዕራብ የሚመጣ ነፋስ ወደ ምሥራቅ ይነፍሳል። ሆኖም ጳውሎስ ወደ ምዕራብ ሲጓዝ የሮማውያንን መንገዶች ተጠቅሞ በየብስ መሄድን ይመርጥ ነበር። ጳውሎስ ሁለተኛውንና ሦስተኛውን ሚስዮናዊ ጉዞውን ያደራጀው ይህን ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ነበር። (የሐዋርያት ሥራ 15:36-41፤ 16:6-8፤ 17:1, 10፤ 18:22, 23፤ 19:1)a በ59 ከክርስቶስ ልደት በኋላ ገደማ፣ ጳውሎስ በአፒያን ዌይ ተጠቅሞ ወደ ሮም በመሄድ፣ ከሮም በስተ ደቡብ ምሥራቅ 74 ኪሎ ሜትር ርቆ በሚገኘው ሕዝብ የሚበዛበት የአፒ አደባባይ ወይም አፍዩስ ፋሩስ ላይ ከእምነት ባልደረቦቹ ጋር ተገናኝቷል። ሌሎች የእምነት አጋሮቹ ደግሞ ከዚህ ሥፍራ 14 ኪሎ ሜትር ወደ ሮም ቀረብ ብሎ በሚገኝ ሦስት ማደሪያ በተባለ ማረፊያ ቦታ ላይ ይጠብቁት ነበር። (የሐዋርያት ሥራ 28:13-15) በ60 ከክርስቶስ ልደት በኋላ ገደማ ጳውሎስ ምሥራቹ በዘመኑ በነበረው “ዓለም ዙሪያ” እንደተሰበከ ተናግሯል። (ቈላስይስ 1:6, 23) በዚያን ጊዜ የነበሩት መንገዶች ለዚህ ውጤት የበኩላቸውን ድርሻ አበርክተዋል።
-
-
ለጥንቱ የምህንድስና ጥበብ ቅርስ የሆኑት የሮማውያን መንገዶችመጠበቂያ ግንብ—2006 | ጥቅምት 15
-
-
[በገጽ 17 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
ጳውሎስ ሕዝብ በሚበዛበት በአፒ አደባባይ ወይም በአፍዩስ ፋሩስ ከእምነት ባልደረቦቹ ጋር ተገናኝቷል
-