የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • በጥቂቶች ተጠቅሞ ብዙኃኑን መመገብ
    መጠበቂያ ግንብ—2013 | ሐምሌ 15
    • 8. በጴንጤቆስጤ ወቅት አማኝ የሆኑት ሰዎች ክርስቶስ የሚጠቀምበት መስመር ማን እንደሆነ በሚገባ እንደተገነዘቡ ያሳዩት እንዴት ነው?

      8 ከሞት የተነሳው ክርስቶስ በ33 ዓ.ም. ከዋለው የጴንጤቆስጤ በዓል አንስቶ የተቀሩትን ቅቡዓን ደቀ መዛሙርቱን ለመመገብ ሐዋርያቱን የሐሳብ ማስተላለፊያ መስመር አድርጎ መጠቀም ጀምሯል። (የሐዋርያት ሥራ 2:41, 42⁠ን አንብብ።) በዚያን ዕለት ክርስትናን ተቀብለው በመንፈስ የተቀቡ አይሁዶች (ወደ ይሁዲነት የተለወጡ አሕዛብን ይጨምራል) ይህ መስመር ማን እንደሆነ በሚገባ ተገንዝበው ነበር። በመሆኑም ያለ ምንም ማቅማማት “[የሐዋርያቱን] ትምህርት በትኩረት መከታተላቸውን ቀጠሉ።” አንድ ምሁር እንደተናገሩት ከሆነ “በትኩረት መከታተላቸውን ቀጠሉ” ተብሎ የተተረጎመው የግሪክኛ ግስ “አንድን ድርጊት በጽናትና ያለ ምንም ማወላወል በታማኝነት መደገፍ” የሚል ፍቺም ሊያስተላልፍ ይችላል። አዲሶቹ አማኞች መንፈሳዊ ምግብ የማግኘት ከፍተኛ ፍላጎት ነበራቸው፤ ደግሞም ይህን ምግብ ከየት ማግኘት እንደሚችሉ ጠንቅቀው ያውቁ ነበር። በዝግጅቱ ላይ የማይናወጥ እምነት ስለነበራቸው ኢየሱስ የተናገራቸውንና ያደረጋቸውን ነገሮች አስመልክቶ እንዲሁም ከኢየሱስ ጋር የተያያዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በተመለከተ ግልጽ ማብራሪያ ሲፈልጉ ፊታቸውን የሚያዞሩት ወደ ሐዋርያቱ ነበር።c—ሥራ 2:22-36

  • በጥቂቶች ተጠቅሞ ብዙኃኑን መመገብ
    መጠበቂያ ግንብ—2013 | ሐምሌ 15
    • c አንቀጽ 8፦ አዲሶቹ አማኞች “[የሐዋርያቱን] ትምህርት በትኩረት መከታተላቸውን ቀጠሉ” መባሉ ሐዋርያት መደበኛ በሆነ መንገድ ያስተምሩ እንደነበረ ያሳያል። አንዳንዶቹ የሐዋርያት ትምህርቶች በመንፈስ መሪነት በተጻፉት የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ ተመዝግበው ይገኛሉ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ