የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “አምላክን እንደ ገዢያችን አድርገን ልንታዘዝ ይገባል”
    ‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
    • 7, 8. መልአኩ የሰጣቸው ትእዛዝ በሐዋርያቱ ላይ ምን በጎ ተጽዕኖ አሳድሮ ሊሆን ይችላል? እኛስ ራሳችንን ምን ብለን መጠየቃችን አስፈላጊ ነው?

      7 ሐዋርያቱ እስር ቤት ሆነው ፍርዳቸውን ሲጠባበቁ፣ በጠላቶቻቸው እጅ ተገድለው ሰማዕት እንደሚሆኑ አስበው ሊሆን ይችላል። (ማቴ. 24:9) ሆኖም ሌሊት ላይ አንድ ፈጽሞ ያልተጠበቀ ነገር ተከሰተ፤ “የይሖዋ መልአክ የእስር ቤቱን በሮች” ከፈተ።b (ሥራ 5:19) ከዚያም መልአኩ “በቤተ መቅደሱ ቆማችሁ . . . መናገራችሁን ቀጥሉ” በማለት ግልጽ መመሪያ ሰጣቸው። (ሥራ 5:20) ይህ ትእዛዝ ሐዋርያቱ ያደረጉት ነገር ትክክለኛ መሆኑን አረጋግጦላቸው መሆን አለበት። በተጨማሪም መልአኩ የተናገረው ሐሳብ ሐዋርያቱ ምንም ነገር ቢያጋጥማቸው በአቋማቸው እንዲጸኑ ሳያበረታታቸው አይቀርም። “ንጋት ላይ ወደ ቤተ መቅደሱ ገብተው” በጠንካራ እምነትና በድፍረት “ያስተምሩ ጀመር።”—ሥራ 5:21

  • “አምላክን እንደ ገዢያችን አድርገን ልንታዘዝ ይገባል”
    ‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
    • b በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ መላእክት በቀጥታ ከተጠቀሱባቸው 20 የሚያክሉ ቦታዎች ይህ የመጀመሪያው ነው። ከዚህ በፊት በሐዋርያት ሥራ 1:10 ላይ መላእክት “ነጫጭ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች” ተብለው በተዘዋዋሪ መንገድ ተጠቅሰዋል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ