-
“አምላክን እንደ ገዢያችን አድርገን ልንታዘዝ ይገባል”‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
-
-
ሐዋርያት እንዳደረጉት ሁሉ እኛም “ከቤት ወደ ቤት” እየሄድን እንሰብካለን
16. ሐዋርያቱ በሚገባ ለመመሥከር ቆርጠው እንደነበር ያሳዩት እንዴት ነው? እኛስ ሐዋርያቱ የተጠቀሙበትን የስብከት ዘዴ እየኮረጅን ያለነው እንዴት ነው?
16 ሐዋርያቱ ወዲያውኑ ወደ ስብከቱ ሥራቸው ተመለሱ። ያለምንም ፍርሃት “በየቀኑ በቤተ መቅደስም ሆነ ከቤት ወደ ቤት እየሄዱ ስለ ክርስቶስ . . . የሚናገረውን ምሥራች . . . ማወጃቸውን ቀጠሉ።”d (ሥራ 5:42) እነዚህ ቀናተኛ ሰባኪዎች በሚገባ ለመመሥከር ቆርጠው ነበር። ኢየሱስ ክርስቶስ ባዘዛቸው መሠረት ከቤት ወደ ቤት እየሄዱ መልእክቱን ያውጁ እንደነበር ልብ በል። (ማቴ. 10:7, 11-14) በትምህርታቸው ኢየሩሳሌምን ሊሞሉ የቻሉት በዚህ መንገድ እንደነበር ምንም ጥርጥር የለውም። በዛሬው ጊዜም የይሖዋ ምሥክሮች የሚታወቁት ሐዋርያቱ በተጠቀሙበት በዚህ የስብከት ዘዴ ነው። ክልላችን ውስጥ እያንዳንዱን ቤት ማንኳኳታችን ምሥራቹን በሚገባ ለመመሥከር ያለንን ፍላጎት ያሳያል፤ ምክንያቱም ይህ የስብከት ዘዴ እያንዳንዱ ሰው ምሥራቹን የሚሰማበት አጋጣሚ እንዲያገኝ ያደርጋል። በእርግጥ ይሖዋ ከቤት ወደ ቤት በመሄድ የምናከናውነውን አገልግሎት ባርኮታል? አዎ፣ ባርኮታል! በዚህ በመጨረሻው ዘመን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ለመንግሥቱ መልእክት ጥሩ ምላሽ እየሰጡ ነው፤ ከእነዚህ መካከል ደግሞ ብዙዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ምሥራቹን የሰሙት የይሖዋ ምሥክሮች ቤታቸውን ባንኳኩበት ወቅት ነው።
-