የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “አንቺ በጣም ውብ ሴት ነሽ”
    መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2017 | ቁጥር 3
    • አብርሃም በደስታ ተሞልቶ ወደ ሣራ መጣ። የገጠመውን ሁኔታ ማመን አልቻለም። የሚያመልኩት አምላካቸው በመልአኩ አማካኝነት ተገልጦለት አነጋገረው! ሣራ ባሏን ዓይን ዓይኑን እያየች “ምን አለህ? እባክህ ንገረኝ!” በማለት ስትጠይቀው በዓይነ ሕሊናህ ይታይህ። አብርሃም ምናልባትም መጀመሪያ ላይ አረፍ ብሎ ሐሳቡን ሰብሰብ ካደረገ በኋላ ይሖዋ ምን እንዳለው ነገራት፦ “ከአገርህ ወጥተህ፣ ከዘመዶችህም ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ሂድ።” (የሐዋርያት ሥራ 7:2, 3) ትንሽ ከተረጋጉ በኋላ ግን ይሖዋ በሰጣቸው መመሪያ ላይ በቁም ነገር ማሰብ ጀመሩ። የተደላደለና የተመቻቸ ኑሯቸውን ትተው የዘላን ዓይነት ሕይወት ሊኖሩ ነው! ሣራ ምን ምላሽ ትሰጥ ይሆን? አብርሃም የሣራን ምላሽ ለመስማት ጓጉቶ እንደሚሆን አያጠራጥርም። አብርሃም ሕይወታቸውን የሚለውጥ እንዲህ ያለ ከባድ ውሳኔ ሲያደርግ በፈቃደኝነት ትተባበረው ይሆን?

      ሣራን ያጋጠማት ሁኔታ እኛን እንደማያጋጥመን ይሰማን ይሆናል። ‘መቼም አምላክ እኔን ወይም ባለቤቴን እንዲህ ዓይነት ነገር እንድናደርግ ጠይቆን አያውቅም!’ ብለን እናስብ ይሆናል። ይሁን እንጂ ከዚህ ጋር የሚመሳሰል ውሳኔ ማድረግ የሚጠይቅ ሁኔታ ሊያጋጥመን ይችላል። የምንኖርበት ዓለም ለቁሳዊ ነገሮች ከልክ ያለፈ ቦታ የሚሰጥ ዓለም ነው፤ እኛንም ቢሆን ለምቾታችን፣ ለንብረቶቻችን ወይም የተረጋጋ ሕይወት ለመኖር ቅድሚያ እንድንሰጥ ተጽዕኖ ሊያሳድርብን ይችላል። ሆኖም መጽሐፍ ቅዱስ ከዚህ የተለየ ውሳኔ እንድናደርግ ይኸውም ለመንፈሳዊ ነገሮች ቅድሚያ እንድንሰጥና ራሳችንን ከማስደሰት ይልቅ አምላክን ለማስደሰት ጥረት እንድናደርግ ያበረታታናል። (ማቴዎስ 6:33) ሣራ ባደረገችው ውሳኔ ላይ ስናሰላስል ‘እኔስ በሕይወቴ ውስጥ ምን ዓይነት ውሳኔዎችን አደርጋለሁ?’ ብለን ራሳችንን መጠየቅ እንችላለን።

  • “አንቺ በጣም ውብ ሴት ነሽ”
    መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2017 | ቁጥር 3
    • ሣራ ስለምትለያቸው ቤተሰቦቿስ ምን ማለት ይቻላል? አምላክ ‘ከአገራቸው ወጥተው፣ ከዘመዶቻቸውም ተለይተው እንዲሄዱ’ የሰጣቸው ትእዛዝ በተለይ ለሣራ ከባድ ሆኖባት መሆን አለበት። አፍቃሪ ሴት እንደመሆኗ መጠን በጣም የምትቀርባቸው ወንድሞች፣ እህቶች፣ የወንድምና የእህት ልጆች እንዲሁም አክስቶችና አጎቶች ይኖሯት ይሆናል፤ እነዚህን በሙሉ ዳግመኛ ላታያቸው ትችላለች። ቢሆንም፣ ሣራ ያላንዳች ማመንታት ለጉዞው ዝግጅት ማድረጓን ቀጠለች።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ