-
“ስለ ኢየሱስ የሚገልጸውን ምሥራች” ማወጅ‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
-
-
3. (ሀ) ፊልጶስ ማን ነው? (ለ) የስብከቱ ሥራ በሰማርያ እምብዛም ያልተስፋፋው ለምን ነበር? ይሁንና ኢየሱስ በዚያ አካባቢ ምን እንደሚሆን አስቀድሞ ተናግሯል?
3 ‘ከተበተኑት ደቀ መዛሙርት’ አንዱ ፊልጶስ ነው።a (ሥራ 8:4፤ “‘ወንጌላዊው’ ፊልጶስ” የሚለውን ሣጥን ተመልከት።) ፊልጶስ የሄደው ወደ ሰማርያ ነው፤ የሰማርያ ከተማ ከስብከቱ ሥራ አንጻር በአብዛኛው ያልተነካ ክልል ነበር። ምክንያቱም በአንድ ወቅት ኢየሱስ ለሐዋርያቱ “ወደ ማንኛውም የሳምራውያን [ከተማ] አትግቡ፤ ከዚህ ይልቅ ከእስራኤል ቤት ወደጠፉት በጎች ብቻ ሂዱ” የሚል መመሪያ ሰጥቷቸው ነበር። (ማቴ. 10:5, 6) ሆኖም ኢየሱስ ከጊዜ በኋላ በሰማርያ ምሥራቹ በሚገባ እንደሚሰበክ ያውቅ ነበር፤ ወደ ሰማይ ከማረጉ በፊት “በኢየሩሳሌም፣ በመላው ይሁዳና በሰማርያ እንዲሁም እስከ ምድር ዳር ድረስ ምሥክሮቼ ትሆናላችሁ” ያለው ለዚህ ነው።—ሥራ 1:8
-