የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ጉባኤው “ሰላም አገኘ”
    ‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
    • 1, 2. ሳኦል በደማስቆ ምን ለማድረግ አቅዷል?

      በቁጣ የተሞሉት መንገደኞች ወደ ደማስቆ እየተቃረቡ ነው፤ እዚያ ደርሰው የተላኩበትን ዓላማ እስኪያስፈጽሙ ቸኩለዋል። የክፋት ውጥናቸው ይህ ነው፦ በሕዝቡ ዘንድ የሚጠሉትን የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ከቤታቸው ጎትተው ማውጣት፣ ማሰር፣ ማዋረድ ከዚያም በኢየሩሳሌም ወደሚገኘው የሳንሄድሪን ሸንጎ ወስደው አይቀጡ ቅጣት ማስቀጣት።

      2 የቡድኑ መሪ ሳኦል የተባለ ሰው ነው፤ ቀድሞውንም ቢሆን የንጹሕ ሰው ደም እጁ ላይ አለ።a ከጥቂት ጊዜ በፊት፣ በቅናት ያበዱት ባልንጀሮቹ ታማኙን የኢየሱስ ደቀ መዝሙር እስጢፋኖስን በድንጋይ ወግረው ሲገድሉ የድርጊታቸው ተባባሪ ነበር። (ሥራ 7:57 እስከ 8:1) በኋላ ላይ ሳኦል በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን የኢየሱስ ተከታዮች ማሳደድ ጀመረ፤ ሆኖም ይህ ስላላረካው የስደቱን እሳት በሌሎች ቦታዎችም ለማቀጣጠል ቆርጦ ተነሳ፤ የዚህ ዘመቻ ቀንደኛ መሪም ሆነ። ዓላማው፣ ‘የጌታ መንገድ’ ተብሎ የሚጠራውን እንደ መቅሰፍት የሚታይ ኑፋቄ ጠራርጎ ማጥፋት ነው።—ሥራ 9:1, 2፤ “ሳኦል በደማስቆ የተሰጠው ሥልጣን” የሚለውን ሣጥን ተመልከት።

  • ጉባኤው “ሰላም አገኘ”
    ‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ