የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ጉባኤው “ሰላም አገኘ”
    ‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
    • 12 ሐናንያ የተሰጠውን ተልእኮ በታዛዥነት በመቀበሉ ተባርኳል። የተጣለብህ ኃላፊነት አስጨናቂ በሚሆንበት ጊዜም እንኳ በሚገባ እንድትመሠክር የተሰጠህን ትእዛዝ ተግባራዊ ታደርጋለህ? ለምሳሌ አንዳንዶች፣ ከቤት ወደ ቤት ሄደው የማያውቁትን ሰው ማነጋገር ያስጨንቃቸዋል። ሌሎች ደግሞ በንግድ ቦታዎች፣ መንገድ ላይ፣ በስልክ ወይም በደብዳቤ መመሥከር በጣም ከባድ ሆኖ ይታያቸዋል። ሐናንያ የተሰማውን ፍርሃት አሸንፏል፤ በውጤቱም ሳኦል መንፈስ ቅዱስን እንዲቀበል የመርዳት ልዩ መብት አግኝቷል።b ሐናንያ በኢየሱስ በመታመኑና ሳኦልን እንደ ወንድሙ አድርጎ በመቁጠሩ ስኬታማ ሊሆን ችሏል። እኛም ልክ እንደ ሐናንያ ፍርሃታችንን ማሸነፍ ከፈለግን ኢየሱስ የስብከቱን ሥራ እየመራ እንዳለ እንተማመን፤ ለሰዎች አዘኔታ ይኑረን፤ እንዲሁም አስፈሪ የሚመስሉ ሰዎችም እንኳ ወደፊት ወንድሞቻችን ሊሆኑ እንደሚችሉ እናስብ።—ማቴ. 9:36

  • ጉባኤው “ሰላም አገኘ”
    ‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
    • b በመሠረቱ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችን ለሌሎች የመስጠት ሥልጣን የነበራቸው ሐዋርያት ናቸው። በዚህ ጊዜ ግን ኢየሱስ ይህን ሥልጣን ለሐናንያ የሰጠው ይመስላል፤ በመሆኑም በዚህ ለየት ያለ ሁኔታ ሳኦል የመንፈስ ቅዱስን ስጦታዎች የተቀበለው ከሐናንያ ነው። ሳኦል ክርስትናን ከተቀበለ በኋላ ረዘም ላለ ጊዜ ከ12ቱ ሐዋርያት ጋር አልተገናኘም። ይሁንና በእነዚህ ጊዜያት ሁሉ የስብከቱን ሥራ በትጋት ሲያከናውን እንደቆየ ግልጽ ነው። በመሆኑም ኢየሱስ፣ ሳኦል የስብከት ተልእኮውን በጽናት ለመወጣት የሚያስችለውን ኃይል እንዲያገኝ ፈልጎ እንደነበር መረዳት ይቻላል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ