የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 1 | አታዳላ
    መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2022 | ቁጥር 1
    • የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፦

      “አምላክ እንደማያዳላ በእርግጥ አስተዋልኩ፤ ከዚህ ይልቅ ከየትኛውም ብሔር ቢሆን እሱን የሚፈራና ትክክል የሆነውን ነገር የሚያደርግ ሰው በእሱ ዘንድ ተቀባይነት አለው።”—የሐዋርያት ሥራ 10:34, 35

      ምን ማለት ነው?

      ይሖዋa አምላክ በዜግነታችን፣ በዘራችን፣ በቆዳ ቀለማችን ወይም በባሕላችን አይገምተንም። ከዚህ ይልቅ የሚያተኩረው በውስጣዊ ማንነታችን ላይ ነው። በእርግጥም “ሰው የሚያየው ውጫዊ ገጽታን ነው፤ ይሖዋ ግን የሚያየው ልብን ነው።”—1 ሳሙኤል 16:7

  • 1 | አታዳላ
    መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2022 | ቁጥር 1
    • መጀመሪያ ላይ፣ ታይተስ በልቡ ውስጥ ያለውን ጥላቻ ማሸነፍ ከብዶት ነበር። “በአመለካከቴም ሆነ በአኗኗሬ ላይ ለውጥ ማድረግ አስቸጋሪ ሆኖብኝ ነበር” ብሏል። ሆኖም በሐዋርያት ሥራ 10:34, 35 ላይ ያገኘው ትምህርት በጣም ጠቅሞታል፤ ጥቅሱ አምላክ እንደማያዳላ ይናገራል።

      ታዲያ ውጤቱ ምን ሆነ? ታይተስ እንዲህ ብሏል፦ “የይሖዋ ምሥክሮች የዘርና የቀለም ልዩነት ሳይበግራቸው እርስ በርስ እንደሚዋደዱ መመልከቴ እውነተኛውን ሃይማኖት እንደሚከተሉ እርግጠኛ እንድሆን አድርጎኛል። ተጠምቄ የይሖዋ ምሥክር ከመሆኔ በፊት እንኳ የጉባኤ አባል የሆነ አንድ ነጭ ሰው እቤቱ ምግብ ጋብዞኛል። ይህ ለእኔ እንደ ሕልም ነበር። ከነጮች ጋር እቤታቸው ቁጭ ብዬ ምግብ ልበላ ቀርቶ በሰላም ጎን ለጎን ተቀምጬ አላውቅም። አሁን ግን የእውነተኛው የዓለም አቀፍ የወንድማማች ማኅበር አባል ሆኛለሁ።”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ