የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g21 ቁጥር 1 ገጽ 6-7
  • ከሌሎች ጋር በሰላም ለመኖር የሚረዳ መመሪያ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከሌሎች ጋር በሰላም ለመኖር የሚረዳ መመሪያ
  • ንቁ!—2021
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ይቅር ባይ ሁን
  • ትሑትና ሰው አክባሪ ሁን
  • አታዳላ
  • ገር ሁን
  • ለጋስና አመስጋኝ ሁን
  • በልግስና መስጠት ደስታ ያስገኛል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2018
  • ‘እርስ በርስ በነፃ ይቅር መባባላችሁን ቀጥሉ’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
  • እርስ በርስ በነፃ ይቅር ተባባሉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • ስኬታማ ለመሆን የሚረዱ ስድስት መንገዶች
    ንቁ!—2008
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2021
g21 ቁጥር 1 ገጽ 6-7
ራት እንዲበሉ እንግዶችን ቤቱ የጋበዘ አንድ ቤተሰብ።

ከሌሎች ጋር በሰላም ለመኖር የሚረዳ መመሪያ

ፈጣሪያችን፣ ከሌሎች ጋር በሰላም መኖር የምንችልበትን መንገድ ነግሮናል፤ ይህ ምክር፣ ቤት ውስጥ፣ በሥራ ቦታ ወይም ከጓደኞቻችን ጋር ባለን ግንኙነት ይጠቅመናል። እሱ ከሰጠን ጥበብ ያዘሉ ምክሮች መካከል ብዙዎች ጠቃሚ ሆነው ያገኟቸውን አንዳንድ ምክሮች እንመልከት።

ይቅር ባይ ሁን

“አንዱ በሌላው ላይ ቅር የተሰኘበት ነገር ቢኖረው እንኳ . . . በነፃ ይቅር መባባላችሁን ቀጥሉ።”—ቆላስይስ 3:13

ስህተት የማይሠራ የለም። ሌሎች እኛን ሊያስቀይሙን፣ እኛም ሌሎችን ልናስቀይም እንችላለን። ያም ሆነ ይህ፣ ሁላችንም ይቅር ማለት ወይም ይቅር መባል የሚያስፈልገን ጊዜ ይኖራል። ይቅር እንላለን ሲባል፣ በበደለን ሰው ላይ ያለንን ቅያሜ እንተወዋለን ማለት ነው። “በክፉ ፋንታ ክፉ” አንመልስም፤ እንዲሁም ግለሰቡ ያደረሰብንን በደል አሥር ጊዜ አናነሳበትም። (ሮም 12:17) ሆኖም ስሜታችን በጣም ከተጎዳና ጉዳዩን ከአእምሯችን ማውጣት ከተቸገርንስ? እንዲህ ከሆነ፣ ግለሰቡን ብቻውን በአክብሮት ልናነጋግረው ይገባል። ግባችን ሰላም መፍጠር እንጂ እሱ ጥፋተኛ መሆኑን ማሳመን መሆን የለበትም።—ሮም 12:18

ትሑትና ሰው አክባሪ ሁን

“ሌሎች ከእናንተ እንደሚበልጡ በትሕትና አስቡ።”—ፊልጵስዩስ 2:3

ትሑትና ሰው አክባሪ ከሆንን፣ ሰዎች ከእኛ ጋር መሆን ያስደስታቸዋል። በደግነትና በአሳቢነት እንደምንይዛቸው እንዲሁም ሆን ብለን እነሱን የሚያስቀይም ነገር እንደማናደርግ ያውቃሉ። ከሌሎች እንደምንበልጥ የምናስብ ወይም እኔ ያልኩት ካልሆነ ብለን ድርቅ የምንል ከሆነ ከሌሎች ጋር መጋጨታችን አይቀርም። ሰዎች ስለሚርቁን ጓደኛ ማግኘት እንቸገራለን።

አታዳላ

“አምላክ [አያዳላም]፤ ከዚህ ይልቅ ከየትኛውም ብሔር ቢሆን እሱን የሚፈራና ትክክል የሆነውን ነገር የሚያደርግ ሰው በእሱ ዘንድ ተቀባይነት አለው።”—የሐዋርያት ሥራ 10:34, 35

ፈጣሪያችን የሰዎችን ዘር፣ ቋንቋ፣ የኑሮ ደረጃ ወይም የቆዳ ቀለም አይቶ አያዳላም። እሱ “የሰውን ወገኖች በሙሉ” የፈጠረው “ከአንድ ሰው” ነው። (የሐዋርያት ሥራ 17:26) በሌላ አባባል፣ ሰዎች ሁሉ ወንድማማቾችና እህትማማቾች ናቸው። ሰዎችን ሁሉ በአክብሮትና በደግነት የምንይዝ ከሆነ ደስተኛ እንዲሆኑ እናደርጋለን፤ እኛ ራሳችን እንደሰታለን፣ ፈጣሪያችንንም እናስደስታለን።

ገር ሁን

“ገርነትን . . . ልበሱ።”—ቆላስይስ 3:12

ገር ከሆንን ሰዎች ከእኛ ጋር መሆን ይቀላቸዋል። እኛን ማናገር፣ ሌላው ቀርቶ ስህተት ስንሠራ ማረም አይከብዳቸውም፤ ምክንያቱም እንዲህ በማድረጋቸው እንደማንቆጣ ያውቃሉ። አንድ ሰው በእኛ ላይ በሚቆጣበት ጊዜ ደግሞ በገርነት ካናገርነው ቁጣው ሊበርድለት ይችላል። ምሳሌ 15:1 “የለዘበ መልስ ቁጣን ያበርዳል፤ ክፉ ቃል ግን ቁጣን ያነሳሳል” ይላል።

ለጋስና አመስጋኝ ሁን

“ከመቀበል ይልቅ መስጠት የበለጠ ደስታ ያስገኛል።”—የሐዋርያት ሥራ 20:35

በዛሬው ጊዜ ብዙ ሰዎች ስስታም ናቸው፤ የሚያስቡት ስለ ራሳቸው ብቻ ነው። እውነተኛ ደስታ የሚገኘው ግን ለጋስ በመሆን ነው። (ሉቃስ 6:38) በልግስና የሚሰጡ ሰዎች ደስተኞች ናቸው፤ ምክንያቱም ከቁሳቁስ ይልቅ ሰዎችን ይወዳሉ። ለሰዎች እንዲህ ዓይነት ፍቅር ስላላቸው እነሱም የሆነ ነገር ሲደረግላቸው አድናቂ ናቸው፤ ላደረገላቸው ሰው ምስጋናቸውን ይገልጻሉ። (ቆላስይስ 3:15) እንዲህ ብለህ ራስህን ጠይቅ፦ ‘ከምን ዓይነት ሰው ጋር መሆን ነው የሚያስደስተኝ? ስስታምና ምስጋና ቢስ ከሆነ ሰው ጋር ነው ወይስ ለጋስና አመስጋኝ ከሆነ ሰው ጋር?’ ይህ ምን ያሳያል? ሌሎች እንዲሆኑ የምትፈልገውን አንተ ራስህ ሆነህ መገኘት አለብህ።—ማቴዎስ 7:12

አሁን ማንንም ሰው አልንቅም

“መጽሐፍ ቅዱስ ‘ለራሳችሁ ያላችሁ ዓይነት አመለካከት ለሌሎችም ይኑራችሁ፤ . . . ጥበበኞች እንደሆናችሁ አድርጋችሁ አታስቡ’ ይላል።” (ሮም 12:16) “ይህ መመሪያ ኩራትንና ለሌሎች ያለኝን የንቀት አመለካከት እንዳስወግድ ረድቶኛል። አሁን የእኔ ዘር ከሌሎች የበላይ እንደሆነ አድርጌ አላስብም፤ ከእኔ የተለየ ሃይማኖት ያላቸውን ሰዎችም አልንቅም። በተጨማሪም ከሰዎች ጋር በቀላሉ መግባባት ችያለሁ፤ የማገኛቸውን ሰዎች ማነጋገርም የቀድሞውን ያህል አይከብደኝም።”—አሻ

አሻ።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፦

ከሰዎች ጋር ያለህ ግንኙነት እንዲሻሻል የሚረዱ ተጨማሪ ምክሮች ማግኘት ትፈልጋለህ? jw.org የተባለው ድረ ገጽ ላይ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች > ሰላም እና ደስታ > ከሰዎች ጋር ያለን ግንኙነት በሚለው ሥር ተመልከት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ