የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ‘አምላክ አያዳላም’
    ‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
    • 22, 23. የአንጾኪያ ክርስቲያኖች የወንድማማችነት ፍቅራቸውን የሚገልጽ ምን ነገር አድርገዋል? በዛሬው ጊዜ ያሉ የአምላክ ሕዝቦችስ ምን ተመሳሳይ ነገር ያደርጋሉ?

      22 ደቀ መዛሙርቱ “በመለኮታዊ አመራር ለመጀመሪያ ጊዜ ‘ክርስቲያኖች’ ተብለው የተጠሩት በአንጾኪያ ነበር።” (ሥራ 11:26ለ) አምላክ የሰጣቸው ይህ ስም በአኗኗራቸው የክርስቶስን ፈለግ በጥብቅ የሚከተሉትን እነዚህን ሰዎች ጥሩ አድርጎ ይገልጻቸዋል። ከአሕዛብ ወገን የሆኑ ሰዎች ክርስትናን ሲቀበሉ ከአይሁዳውያን ክርስቲያኖች ጋር የጠበቀ ወንድማማችነት መሥርተው ይሆን? በ46 ዓ.ም. ገደማ ታላቅ ረሃብ በተከሰተ ጊዜ ምን እንደሆነ ተመልከት።e በጥንት ዘመን ረሃብ ሲከሰት ይበልጥ የሚጠቁት ድሆች ነበሩ፤ ምክንያቱም ተቀማጭ ገንዘብም ሆነ ምግብ የላቸውም። በይሁዳ ካሉት አይሁዳውያን ክርስቲያኖች ብዙዎቹ ድሆች ሳይሆኑ አይቀሩም፤ በመሆኑም ይህ ረሃብ በተከሰተበት ጊዜ እርዳታ አስፈልጓቸው ነበር። ከአሕዛብ ወገን የመጡትን ጨምሮ በአንጾኪያ የሚገኙት ክርስቲያኖች ይህን ሲያውቁ “በይሁዳ ለሚኖሩ ወንድሞች እርዳታ ለመላክ ወሰኑ።” (ሥራ 11:29) ይህ እውነተኛ የወንድማማችነት ፍቅርን የሚያሳይ ተግባር ነው።

  • ‘አምላክ አያዳላም’
    ‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
    • e አይሁዳዊው ታሪክ ጸሐፊ ጆሴፈስ ይህ “ታላቅ ረሃብ” በንጉሠ ነገሥት ቀላውዴዎስ ዘመነ መንግሥት (41-54 ዓ.ም.) እንደተከሰተ ገልጿል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ