-
ነቅቶ ስለመጠበቅ ከኢየሱስ ሐዋርያት ተማሩመጠበቂያ ግንብ—2012 | ጥር 15
-
-
11, 12. ሄሮድስ፣ በጴጥሮስም ሆነ በሌሎች ክርስቲያኖች ላይ ምን ስደት አደረሰ?
11 በዚያ ወቅት ከነበሩት ሐዋርያት አንዱ የሆነው ጴጥሮስ ልባዊ ጸሎት ማቅረብ የሚያስገኘውን ውጤት ከጊዜ በኋላ በራሱ ሕይወት ለማየት ችሏል። (የሐዋርያት ሥራ 12:1-6ን አንብብ።) በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 12 የመጀመሪያ ቁጥሮች ላይ ሄሮድስ በአይሁዳውያን ዘንድ ተወዳጅነት ለማትረፍ ሲል ክርስቲያኖችን ማሳደድ እንደጀመረ እንመለከታለን። ያዕቆብ፣ ከሐዋርያቱ አንዱ እንደሆነና ከኢየሱስም ጋር በጣም ይቀራረብ እንደነበረ ሄሮድስ ሳያውቅ አይቀርም። በመሆኑም ሄሮድስ “ያዕቆብን በሰይፍ ገደለው።” (ቁጥር 2) በዚህም ምክንያት ጉባኤው ተወዳጅ የሆነ አንድ ሐዋርያ አጣ። ይህ ለወንድሞች እንዴት ያለ ትልቅ ፈተና ነበር!
-
-
ነቅቶ ስለመጠበቅ ከኢየሱስ ሐዋርያት ተማሩመጠበቂያ ግንብ—2012 | ጥር 15
-
-
13, 14. (ሀ) ጴጥሮስ በታሰረበት ወቅት ጉባኤው ምን አደረገ? (ለ) የጴጥሮስ የእምነት ባልንጀሮች በጸሎት ረገድ ከተዉት ምሳሌ ምን ትምህርት ማግኘት እንችላለን?
13 ጉባኤው ምን ማድረግ እንዳለበት በሚገባ ያውቅ ነበር። ቁጥር 5 እንዲህ ይላል፦ “ጴጥሮስ እስር ቤት እንዲቆይ ተደረገ፤ ሆኖም ጉባኤው ስለ እሱ ወደ አምላክ አጥብቆ ይጸልይ ነበር።” አዎ፣ ክርስቲያን ባልንጀሮቹ ስለዚህ ተወዳጅ ወንድማቸው አጥብቀው ልባዊ ጸሎት ያቀርቡ ነበር። የያዕቆብ መገደል ተስፋ እንዲቆርጡ ወይም ጸሎት ምንም ፋይዳ እንደሌለው እንዲሰማቸው አላደረጋቸውም። ከዚህ ይልቅ ይሖዋ ታማኝ አገልጋዮቹ ለሚያቀርቡት ጸሎት ትልቅ ቦታ እንደሚሰጥ ተገንዝበው ነበር። አገልጋዮቹ የሚያቀርቧቸው ጸሎቶች ከፈቃዱ ጋር የሚስማሙ ከሆነ መልስ ይሰጣል።—ዕብ. 13:18, 19፤ ያዕ. 5:16
14 የጴጥሮስ የእምነት ባልንጀሮች ካደረጉት ነገር ምን ትምህርት ልናገኝ እንችላለን? ነቅቶ መጠበቅ ለራሳችን ብቻ ሳይሆን ለወንድሞቻችንና ለእህቶቻችንም ጭምር መጸለይን ያካትታል። (ኤፌ. 6:18) መከራ እየደረሰባቸው ስላሉ የእምነት ባልንጀሮቻችን የሰማችሁት ነገር አለ? አንዳንዶቹ ስደት እየደረሰባቸው ወይም ከመንግሥት እገዳ ተጥሎባቸው አሊያም የተፈጥሮ አደጋ ደርሶባቸው ይሆናል። ታዲያ እነዚህን ወንድሞች አስመልክታችሁ ለምን ከልብ የመነጨ ጸሎት አታቀርቡም? እምብዛም ጎልቶ የማይታይ መከራ ተቋቁመው የሚኖሩ ሌሎች ክርስቲያኖች እንዳሉም ታውቁ ይሆናል። እነዚህ ክርስቲያኖች ከቤተሰብ ችግር፣ ከተስፋ መቁረጥ ወይም እምነትን ከሚፈታተን ሌላ ችግር ጋር እየታገሉ ይሆናል። ‘ጸሎት ሰሚ’ የሆነውን ይሖዋን ከማነጋገራችሁ በፊት፣ ስማቸውን ጠቅሳችሁ ልትጸልዩላቸው የምትችሏቸውን ግለሰቦች ለማስታወስ ለምን ቆም ብላችሁ አታስቡም?—መዝ. 65:2
-