የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “በደስታና በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ”
    ‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
    • 1, 2. በርናባስና ሳኦል ሊያደርጉት ያሰቡትን ጉዞ ለየት የሚያደርገው ምንድን ነው? የሚያከናውኑት ሥራስ የሐዋርያት ሥራ 1:8 ፍጻሜውን እንዲያገኝ አስተዋጽኦ የሚያደርገው እንዴት ነው?

      በአንጾኪያ ያለው ጉባኤ እጅግ የተደሰተበት ዕለት ነው። በዚያ ከነበሩት ነቢያትና አስተማሪዎች መካከል በርናባስና ሳኦል በመንፈስ ቅዱስ ተመረጡ፤ ተልእኳቸው ምሥራቹን ራቅ ወዳሉ ቦታዎች ማድረስ ነው።a (ሥራ 13:1, 2) እውነት ነው፣ ከዚያ በፊትም ቢሆን ብቃት ያላቸው ወንዶች ይላኩ ነበር። ይሁን እንጂ ቀደም ሲል ሚስዮናውያን የተላኩት የክርስትናን እምነት የተቀበሉ ሰዎች ወዳሉባቸው አካባቢዎች ነው። (ሥራ 8:14፤ 11:22) በዚህ ጊዜ ግን በርናባስና ሳኦል አብዛኞቹ ሰዎች ምሥራቹን ወዳልሰሙባቸው ቦታዎች ሊላኩ ነው፤ ዮሐንስ ማርቆስም አብሯቸው ይጓዛል፤ በጉዟቸው ላይ እንደ አገልጋይ ሆኖ ይረዳቸዋል።

      2 ከ14 ዓመት ገደማ በፊት ኢየሱስ ተከታዮቹን “በኢየሩሳሌም፣ በመላው ይሁዳና በሰማርያ እንዲሁም እስከ ምድር ዳር ድረስ ምሥክሮቼ ትሆናላችሁ” ብሏቸው ነበር። (ሥራ 1:8) በርናባስና ሳኦል ሚስዮናዊ ሆነው እንዲያገለግሉ መሾማቸው ኢየሱስ የተናገረው ትንቢት ፍጻሜውን እንዲያገኝ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል!b

  • “በደስታና በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ”
    ‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
    • 4. (ሀ) በርናባስና ሳኦል የተመረጡት እንዴት ነው? የእምነት ባልንጀሮቻቸውስ በእነሱ መመረጥ ምን ተሰማቸው? (ለ) ቲኦክራሲያዊ ኃላፊነቶችን ለሚቀበሉ ወንድሞች ድጋፍ መስጠት የምንችለው እንዴት ነው?

      4 ይሁን እንጂ መንፈስ ቅዱስ ‘ለአንድ ሥራ እንዲለዩ’ ከሌሎቹ ሁሉ በርናባስንና ሳኦልን የመረጠው ለምንድን ነው? (ሥራ 13:2) መጽሐፍ ቅዱስ ምክንያቱን አይገልጽም። የምናውቀው ነገር ቢኖር እነዚህ ሰዎች የተመረጡት መንፈስ ቅዱስ በሰጠው መመሪያ መሠረት መሆኑን ነው። በአንጾኪያ የነበሩት ነቢያትና አስተማሪዎች ውሳኔውን ለመቀበል አንገራግረው እንደነበር የሚጠቁም ምንም ነገር አናገኝም። ከዚህ ይልቅ የእነሱን መመረጥ ሙሉ በሙሉ ደግፈዋል። ዘገባው “ከጾሙና ከጸለዩ በኋላ እጃቸውን ጫኑባቸው፤ ከዚያም አሰናበቷቸው” ይላል፤ በርናባስና ሳኦል መንፈሳዊ ወንድሞቻቸው ምንም የቅናት ስሜት ሳያድርባቸው ሲያሰናብቷቸው ምን ያህል ተበረታተው እንደሚሆን አስብ። (ሥራ 13:3) እኛም ቲኦክራሲያዊ ኃላፊነቶች የሚሰጣቸውን ሁሉ ልንደግፋቸው ይገባል፤ ይህም የጉባኤ የበላይ ተመልካች ሆነው የሚሾሙትን ወንድሞች ይጨምራል። እንዲህ ዓይነት መብቶች ባገኙ ወንድሞች ከመቅናት ይልቅ “በሚያከናውኑት ሥራ የተነሳ በፍቅር ለየት ያለ አሳቢነት” ልናሳያቸው ይገባል።—1 ተሰ. 5:13

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ