የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “በደስታና በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ”
    ‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
    • 5. በርናባስና ሳኦል በቆጵሮስ ደሴት የሰበኩት እንዴት ነው?

      5 በርናባስና ሳኦል በአንጾኪያ አቅራቢያ ወደምትገኘው ወደ ሴሌውቅያ ወደብ በእግራቸው ተጓዙ፤ ከዚያም መርከብ ተሳፍረው 200 ኪሎ ሜትር ርቃ ወደምትገኘው የቆጵሮስ ደሴት አቀኑ።d በርናባስ የቆጵሮስ ተወላጅ እንደመሆኑ መጠን ለአገሩ ሰዎች ምሥራቹን ለመንገር ጓጉቶ እንደሚሆን ጥርጥር የለውም። በመጨረሻም በደሴቲቱ ምሥራቃዊ ጠረፍ ወደምትገኘው ስልማና ከተማ ደረሱ፤ ጊዜ ሳያጠፉም “የአምላክን ቃል በአይሁዳውያን ምኩራቦች ማወጅ ጀመሩ።”e (ሥራ 13:5) ከዚህኛው የቆጵሮስ ጫፍ ተነስተው ደግሞ እስከ ሌላኛው ጫፍ ድረስ ተጓዙ፤ እግረ መንገዳቸውን ደሴቲቱ ላይ ባሉ ዋና ዋና ከተሞች ውስጥ ምሥራቹን ሰብከው መሆን አለበት። እነዚህ ሚስዮናውያን የትኛውን መንገድ ይዘው እንደተጓዙ ባናውቅም በጥቅሉ 160 ኪሎ ሜትር ገደማ ሳይጓዙ አልቀሩም!

      በአይሁዳውያን ምኩራቦች ውስጥ

      “ምኩራብ” የሚለው ቃል በቀጥታ ሲተረጎም “መሰብሰብ” ማለት ነው። ይህ ቃል የአይሁዳውያንን ስብሰባ ወይም ጉባኤ ያመለክት ነበር፤ ውሎ አድሮ ግን ስብሰባው የሚካሄድበትን ቦታ ወይም ሕንፃ ለማመልከት ይሠራበት ጀመር።

      በብዙዎች ዘንድ እንደሚታመነው፣ ምኩራቦች መቋቋም የጀመሩት አይሁዳውያን ለ70 ዓመት በባቢሎን በግዞት በነበሩበት ወቅት ወይም ከግዞት እንደተመለሱ ነው። ምኩራቦች ትምህርትና መንፈሳዊ ማበረታቻ የሚሰጥባቸው፣ አምልኮ የሚቀርብባቸው እንዲሁም ቅዱሳን መጻሕፍት የሚነበቡባቸው ቦታዎች ነበሩ። በመጀመሪያው መቶ ዘመን ዓ.ም. በፓለስቲና ምድር ያለ እያንዳንዱ ከተማ የራሱ ምኩራብ ነበረው። ትላልቆቹ ከተሞች ከአንድ በላይ ምኩራቦች ነበሯቸው፤ ኢየሩሳሌም ደግሞ ብዙ ምኩራቦች ነበሯት።

      ከባቢሎን ግዞት በኋላ ወደ ፓለስቲና ምድር የተመለሱት ሁሉም አይሁዳውያን አልነበሩም። ብዙዎቹ አይሁዳውያን ለመነገድ ሲሉ ወደ ሌሎች አገሮች ሄደው ነበር። ቢያንስ በአምስተኛው መቶ ዘመን ዓ.ዓ. አይሁዳውያን በአሦር ግዛት ባሉ 127 አውራጃዎች ውስጥ ይገኙ ነበር። (አስ. 1:1፤ 3:8) ከጊዜ በኋላ ደግሞ በሜድትራንያን ዙሪያ ባሉ ከተሞች በሙሉ መኖር ጀመሩ። እነዚህ አይሁዳውያን “ዳያስፖራ” ወይም የተበተኑ ተብለው ይጠሩ ጀመር፤ እነሱም በሰፈሩበት ቦታ ሁሉ ምኩራቦችን አቋቋሙ።

      በምኩራቦች ውስጥ በየሰንበቱ ሕጉ ይነበብና ይብራራ ነበር። አንባቢው ከፍ ያለ ቦታ ላይ ቆሞ፣ ከመድረኩ ፊት ለፊት እንዲሁም ግራና ቀኝ ለተቀመጡት አድማጮች ያነብላቸዋል። ማንኛውም ቀናተኛ የሆነ አይሁዳዊ ወንድ በማንበብ፣ በመስበክና ማበረታቻ በመስጠት ተሳትፎ ማድረግ ይችላል።

  • “በደስታና በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ”
    ‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
    • d በመጀመሪያው መቶ ዘመን፣ አንድ መርከብ የነፋሱ ሁኔታ ጥሩ ከሆነ በቀን 160 ኪሎ ሜትር ገደማ ይጓዝ ነበር። የአየሩ ሁኔታ አመቺ በማይሆንበት ጊዜ ደግሞ ጉዞው ረዘም ያለ ጊዜ ሊወስድ ይችላል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ