የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “በደስታና በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ”
    ‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
    • 6, 7. (ሀ) ሰርግዮስ ጳውሎስ ማን ነው? በርያሱስ ይህ ሰው ምሥራቹን እንዳይሰማ ሊያከላክል የሞከረውስ ለምንድን ነው? (ለ) ሳኦል፣ በርያሱስ ላስነሳው ተቃውሞ ምላሽ የሰጠው እንዴት ነው?

      6 በመጀመሪያው መቶ ዘመን ቆጵሮስ የሐሰት አምልኮ መናኸሪያ ነበረች። በርናባስና ሳኦል በደሴቲቱ ምዕራባዊ ዳርቻ ወደምትገኘው ወደ ጳፎስ በደረሱ ጊዜ ያጋጠማቸው ሁኔታ ይህን በግልጽ የሚያሳይ ነው። በዚያ “በርያሱስ የተባለ . . . ጠንቋይና ሐሰተኛ ነቢይ” አገኙ። እሱም “ሰርግዮስ ጳውሎስ ከተባለው አስተዋይ የሮም አገረ ገዢ ጋር ነበር።”f በመጀመሪያው መቶ ዘመን የሠለጠኑ ናቸው የሚባሉ በርካታ ሮማውያን ትላልቅ ውሳኔዎች ሲያደርጉ ጠንቋዮችን ወይም ኮከብ ቆጣሪዎችን የማማከር ልማድ ነበራቸው፤ እንደ ሰርግዮስ ጳውሎስ ያሉ “አስተዋይ” ሰዎችም እንኳ ይህን ያደርጉ ነበር። ይሁንና ሰርግዮስ ጳውሎስ የመንግሥቱን ምሥራች ሲሰማ ደስ አለው፤ “የአምላክን ቃል ለመስማት [ጓጓ]።” ይህ ግን በርያሱስን አላስደሰተውም፤ በርያሱስ ‘ኤልማስ’ በመባልም ይታወቅ የነበረ ሲሆን ትርጉሙ “ጠንቋይ” ማለት ነው።—ሥራ 13:6-8

  • “በደስታና በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ”
    ‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
    • f ቆጵሮስ በሮም አገዛዝ ሥር ነበረች። ደሴቲቱን የሚያስተዳድረው አገረ ገዢው ሲሆን በሮም የተሾመ የአካባቢው ባለሥልጣን ነበር።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ