የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ለዘላለም ሕይወት ዝንባሌ ያላቸውን መፈለግ
    መጠበቂያ ግንብ—1991 | ጥር 15
    • 2. በሰው ምሳሌያዊ ልብ ውስጥ ምን ነገር ተተክሎ ይገኛል? ስለዚህስ ጉዳይ በቅዱሳን ጽሑፎች ውስጥ ምን እናነባለን?

      2 እያንዳንዱ ሰው አንድ አይነት ዋነኛ ዝንባሌ ይኖረዋል። በምሳሌያዊ ልቡ ውስጥ ሥር የሰደደ ዝንባሌ ይኖረዋል። (ማቴዎስ 12:34, 35፤ 15:18-20) በዚህም ምክንያት “በልቡ ግን ሠልፍ ነበረ” የሚል ቃል እናነባለን። (መዝሙር 55:21) “የግልፍተኝነት ዝንባሌ ያለው ሰው ብዙ በደል ይፈጽማል” (አዓት) ይላል። በተጨማሪም “እርስ በርሳቸው የመለያየት ዝንባሌ ያላቸው ባልንጀራሞች አሉ፣ ይሁን እንጂ ከወንድም የበለጠ የሚጠጋ ወዳጅ አለ” የሚል ቃል እናነባለን። (ምሳሌ 18:24፤ 29:22 አዓት) ብዙ ሰዎች በጥንትዋ የጵስድያ አንጾኪያ ይኖሩ እንደነበሩት አንዳንድ አሕዛብ መሆናቸው ያስደስታል። ስለ ይሖዋ የደኅንነት ዝግጅት ሲሰሙ ደስ አላቸው። [የይሖዋንም (አዓት)] ቃል አከበሩ። ለዘላለም ሕይወት ትክክለኛ ዝንባሌ ያላቸው ሁሉ አመኑ። [የይሖዋም (አዓት)] ቃል በአገሩ ሁሉ ተስፋፋ።”​—ሥራ 13:44-48

  • ለዘላለም ሕይወት ዝንባሌ ያላቸውን መፈለግ
    መጠበቂያ ግንብ—1991 | ጥር 15
    • 4 ልበ ንጹሐን የተባሉት በውስጣቸው ንጹሕ የሆኑት ናቸው። የአድናቆት፣ የፍቅር፣ የፍላጎትና የዓላማ ንጽሕና አላቸው። (1 ጢሞቴዎስ 1:5) አምላክ ለፍጹም አቋም ጠባቂዎች የሚያደርግላቸውን ሁሉ ለመመልከት ስለሚችሉ አምላክን ያያሉ። (ከዘፀዓት 33:20፤ ኢዮብ 19:26፤ 42:5 ጋር አወዳድር) እዚህ ላይ “ማየት” ተብሎ የተተረጎመው የግሪክኛ ቃል “በዓይነ ልቡና ማየት፣ ማስተዋል፣ ማወቅ” የሚል ትርጉም አለው። ኢየሱስ የአምላክን ባሕርይ ፍጹም በሆነ ሁኔታ ስላንፀባረቀ “ልባቸው ንፁሕ” ሆኖ በክርስቶስና ኃጢአት በሚያስተሠርየው መሥዋዕቱ ያመኑ፣ የኃጢአት ሥርየት ያገኙና ተቀባይነት ያለው አምልኮ ለአምላክ ለማቅረብ የቻሉ ሁሉ የአምላክን ባሕርይ ለማየት ችለዋል። (ዮሐንስ 14:7-9፤ ኤፌሶን 1:7) ቅቡዓን ክርስቲያኖች ሰማያዊ ትንሣዔ አግኝተው አምላክንና ክርስቶስን ፊት ለፊት ማየት ሲችሉ አምላክን ማየታቸው የመጨረሻውን ከፍተኛ ደረጃ ይይዛል። (2 ቆሮንቶስ 1:21, 22፤ 1 ዮሐንስ 3:2) ይሁን እንጂ ልባቸው ንጹሕ የሆኑ ሁሉ በትክክለኛ ዕውቀትና በእውነተኛ አምልኮ አማካኝነት አምላክን ለማየት ይችላሉ። (መዝሙር 24:3, 4፤ 1 ዮሐንስ 3:6፤ 3 ዮሐንስ 11) በሰማይ ወይም በገነቲቱ ምድር የዘላለም ህይወት ለማግኘት ጥሩ ዝንባሌ አላቸው።​—ሉቃስ 23:43፤ 1 ቆሮንቶስ 15:50-57፤ 1 ጴጥሮስ 1:3-5

      5. አንድ ሰው የኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ ተከታይና አማኝ ሊሆን የሚችለው እንዴት ብቻ ነው?

      5 ለዘላለም ሕይወት ትክክለኛ ዝንባሌ የሌላቸው ሁሉ አማኞች አይሆኑም። ማመን አይቻላቸውም። (2 ተሰሎንቄ 3:2) ለመማር ፈቃደኛ ያልሆነና በልብ ውስጥ ያለውን ለማየት የሚችለው ይሖዋ ያልሳበው ማንኛውም ሰው የኢየሱስ ተከታይ ለመሆን አይችልም። (ዮሐንስ 6:41-47) እርግጥ ነው የይሖዋ ምሥክሮች ከቤት ወደ ቤት እየሄዱ በሚሰብኩበት ጊዜ በማንም ሰው ላይ አስቀድመው አይፈርዱም። የሰዎችን ልብ ለማንበብ ስለማይችሉ የስብከታቸውን ውጤት አፍቃሪ ለሆነው አምላክ ይተዋሉ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ