የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ለእምነታችን መከላከያ ማቅረብ
    መጠበቂያ ግንብ—1998 | ታኅሣሥ 1
    • 12. ጳውሎስና በርናባስ በኢቆንዮን በድፍረት እንዲናገሩ ያነሳሷቸው ሁኔታዎች ምን ነበሩ?

      12 በተጨማሪም የጳውሎስንና የበርናባስን ምሳሌ ተመልከት። ሥራ 14:​1, 2 እንዲህ ይላል:- “በኢቆንዮንም እንደ ቀድሞ ወደ አይሁድ ምኵራብ ገብተው ከአይሁድና ከግሪክ ሰዎች ብዙ እስኪያምኑ ድረስ ተናገሩ። ያላመኑት አይሁድ ግን የአሕዛብን ልብ በወንድሞች ላይ አነሣሡ አስከፉም።” ዘ ኒው ኢንግሊሽ ባይብል “ያላመኑት አይሁድ ግን አሕዛብን በመቀስቀስና አእምሯቸውን በመመረዝ ክርስቲያኖችን እንዲጠሉ አደረጉ” ይላል። አይሁዳውያን ተቃዋሚዎች መልእክቱን ለመቀበል እምቢ ማለታቸው ሳይበቃቸው ክርስቲያኖች በአሕዛብ ዘንድ እንዲጠሉ ለማድረግ የስም ማጥፋት ዘመቻ አፋፍመው ነበር።a ለክርስትና እንዴት ያለ ከፍተኛ ጥላቻ ነበራቸው! (ከሥራ 10:​28 ጋር አወዳድር።) ጳውሎስና በርናባስ በዚህ ጊዜ ‘መናገር’ እንዳለባቸው ተሰምቷቸው ነበር፤ አለበለዚያ አዲሶቹ ደቀ መዛሙርት ከሕዝቡ በሚደርስባቸው ተቃውሞ ተስፋ ሊቆርጡ ይችላሉ። “ስለዚህ ጳውሎስና በርናባስ የጌታን ነገር በድፍረት እየተናገሩ እዚያ ብዙ ጊዜ ቆዩ።” ይሖዋም ተአምራታዊ ምልክቶች እንዲያደርጉ ሥልጣን በመስጠት በእርሱ ዘንድ ተቀባይነት ማግኘታቸውን አሳይቷቸዋል። ይህ ደግሞ “እኩሌቶቹ ከአይሁድ እኩሌቶቹም ከሐዋርያት ጋር” እንዲሆኑ አድርጓል።​—⁠ሥራ 14:​3, 4

  • ለእምነታችን መከላከያ ማቅረብ
    መጠበቂያ ግንብ—1998 | ታኅሣሥ 1
    • a ማቲው ሄንሪስ ኮሜንተሪ ኦን ዘ ሆል ባይብል የተባለው መጽሐፍ እንደገለጸው የአይሁድ ተቃዋሚዎች የክርስትናን እምነት የሚቃወሙ አይሁዶች “እምብዛም ወደማያውቋቸው [አሕዛብ] እንኳ ሳይቀር ሥራዬ ብለው በመሄድ ክርስትናን እንዲንቁ ብቻ ሳይሆን ጥላቻ እንዲያድርባቸው ለማድረግ ተንኮል የተሞላ አእምሯቸው ሊያፈልቅ የሚችለውን መጥፎ ነገር ሁሉ ይነግሯቸው ነበር።”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ