የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “ከይሖዋ ባገኙት ሥልጣን በድፍረት” ተናገሩ
    ‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
    • ጳውሎስና በርናባስ በልስጥራ ያለው ሕዝብ እንዳያመልካቸው ሲያከላክሉ። ሕዝቡ የሙዚቃ መሣሪያዎች ሲጫወቱ፣ መሥዋዕት ሲያዘጋጁና በሁለቱ ሰዎች ፊት ሲሰግዱ ይታያል።

      ‘እነዚህን ከንቱ ነገሮች ትታችሁ ሰማይንና ምድርን የፈጠረውን ሕያው አምላክ አምልኩ።’—የሐዋርያት ሥራ 14:15

      11-13. (ሀ) ጳውሎስና በርናባስ ለልስጥራ ነዋሪዎች ምን ብለው ተናገሩ? (ለ) ጳውሎስና በርናባስ ከተናገሩት ነገር የምናገኘው አንዱ ትምህርት ምንድን ነው?

      11 የሕዝቡ ያልተጠበቀ ምላሽ ከፍተኛ ትርምስ ፈጥሯል፤ ጳውሎስና በርናባስ ግን በዚህ ወቅትም እንኳ የአድማጮቻቸውን ልብ ለመንካት የተቻላቸውን ሁሉ ጥረት አድርገዋል። ሉቃስ ያሰፈረው ይህ ዘገባ ምሥራቹን ክርስቲያን ላልሆኑ ሰዎች መስበክ የሚቻልበትን ውጤታማ ዘዴ ያስተምረናል። ጳውሎስና በርናባስ የአድማጮቻቸውን ልብ ለመንካት ምን እንዳሉ ልብ በል፦ “እናንተ ሰዎች፣ እንዲህ የምታደርጉት ለምንድን ነው? እኛም እንደ እናንተው ድክመት ያለብን ሰዎች ነን። ምሥራቹን እያወጅንላችሁ ያለነውም እነዚህን ከንቱ ነገሮች ትታችሁ ሰማይን፣ ምድርን፣ ባሕርንና በውስጣቸው ያሉትን ነገሮች ሁሉ የፈጠረውን ሕያው አምላክ እንድታመልኩ ነው። ባለፉት ትውልዶች፣ ሕዝቦች ሁሉ በራሳቸው መንገድ እንዲሄዱ ፈቀደላቸው፤ ይሁንና ለራሱ ምሥክር ከማቅረብ ወደኋላ አላለም፤ ከሰማይ ዝናብ በማዝነብና ፍሬያማ ወቅቶችን በመስጠት እንዲሁም የተትረፈረፈ ምግብ በማቅረብና ልባችሁን በደስታ በመሙላት መልካም ነገር አድርጓል።”—ሥራ 14:15-17

  • “ከይሖዋ ባገኙት ሥልጣን በድፍረት” ተናገሩ
    ‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
    • 14-16. ጳውሎስና በርናባስ ለልስጥራ ነዋሪዎች ከተናገሩት ነገር የምናገኘው ሁለተኛና ሦስተኛ ትምህርት ምንድን ነው?

      14 ከዚህ ንግግር የምናገኘውን ሁለተኛ ትምህርት ደግሞ እስቲ እንመልከት። ጳውሎስና በርናባስ አቀራረባቸውን እንደ ሁኔታው ያስተካክሉ ነበር። የልስጥራ ነዋሪዎች፣ በኢቆንዮን እንዳሉት አይሁዳውያንና ወደ ይሁዲነት የተለወጡ ሰዎች አይደሉም፤ ስለ ቅዱሳን መጻሕፍትም ሆነ አምላክ ከእስራኤል ብሔር ጋር ስለነበረው ግንኙነት ምንም የሚያውቁት ነገር አልነበረም ማለት ይቻላል። ይሁንና ጳውሎስንና በርናባስን ያዳምጧቸው የነበሩት እነዚህ ሰዎች በግብርና ሙያ የሚተዳደሩ ነበሩ። ልስጥራ ምቹ የሆነ የአየር ጠባይና ለም መሬት የታደለች ነበረች። በመሆኑም ነዋሪዎቿ የፈጣሪን ግሩም ባሕርይ ለማየት የሚያስችል ሰፊ አጋጣሚ ነበራቸው፤ ለምሳሌ ፍሬያማ የሆኑ ወቅቶችና በዙሪያቸው ያሉ ሌሎች ነገሮች ስለ ፈጣሪ የሚያስተምሯቸው ነገሮች አሉ፤ ሚስዮናውያኑም አድማጮቻቸው እንዲያመዛዝኑ ለመርዳት ይህን በጋራ የሚያስማማ ነጥብ ጠቅሰዋል።—ሮም 1:19, 20

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ