-
ይሖዋ ምን ዓይነት አምላክ ነው?ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
3. ይሖዋ እንደሚወደን ያሳየው እንዴት ነው?
ከይሖዋ ባሕርያት መካከል ጎልቶ የሚታየው ፍቅር ነው። እንዲያውም መጽሐፍ ቅዱስ አምላክ ፍቅር እንዳለው ብቻ ሳይሆን ‘አምላክ ራሱ ፍቅር እንደሆነ’ ይናገራል። (1 ዮሐንስ 4:8) ይሖዋ ፍቅሩን የገለጸው በመጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት ብቻ አይደለም፤ የፈጠራቸው ነገሮችም የእሱን ፍቅር ያሳያሉ። (የሐዋርያት ሥራ 14:17ን አንብብ።) እኛን የፈጠረበትን መንገድ እንደ ምሳሌ መውሰድ ትችላለህ። ውብ ቀለማትን የማየት፣ አስደሳች ሙዚቃ የማዳመጥና ጣፋጭ ምግቦችን የማጣጣም ችሎታ ሰጥቶናል። አምላክ ደስተኛ ሆነን እንድንኖር ይፈልጋል።
-
-
በስጦታ ላገኘነው ሕይወት አድናቆት ይኑርህለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
1. ለሕይወት አድናቆት ሊኖረን የሚገባው ለምንድን ነው?
ለሕይወት አድናቆት ሊኖረን የሚገባው አፍቃሪ አባታችን ይሖዋ የሰጠን ስጦታ ስለሆነ ነው። ‘የሕይወት ምንጭ ከእሱ ዘንድ ነው’፤ ሕይወት ያላቸውን ነገሮች በሙሉ የፈጠረው እሱ ነው። (መዝሙር 36:9) “ሕይወትንና እስትንፋስንም ሆነ ማንኛውንም ነገር ለሰው ሁሉ የሚሰጠው” ይሖዋ ነው። (የሐዋርያት ሥራ 17:25, 28) ይሖዋ በሕይወት ለመቀጠል የሚያስፈልጉንን ነገሮችም ይሰጠናል። ከዚህም ባለፈ በሕይወታችን ደስተኛ ለመሆን የሚያስፈልጉንን ነገሮች ያቀርብልናል።—የሐዋርያት ሥራ 14:17ን አንብብ።
-