-
‘የመንግሥተ ሰማያት ቁልፎች’ ምንድን ናቸው?የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
-
-
‘የመንግሥተ ሰማያት ቁልፎች’ ሰዎች “ወደ አምላክ መንግሥት [መግባት]” እንዲችሉ መንገድ የመክፈት ሥልጣንን ያመለክታሉ። (ማቴዎስ 16:19፤ የሐዋርያት ሥራ 14:22)a ኢየሱስ ለጴጥሮስ “የመንግሥተ ሰማያትን ቁልፎች” ሰጥቶታል። ይህም ማለት ጴጥሮስ ታማኝ የሆኑ ሰዎች የአምላክን ቅዱስ መንፈስ በመቀበል ወደ መንግሥተ ሰማያት የመግባት መብት የሚያገኙት እንዴት እንደሆነ የሚገልጸውን መረጃ ለሌሎች የመግለጥ ሥልጣን ተሰጥቶታል ማለት ነው።
-
-
‘የመንግሥተ ሰማያት ቁልፎች’ ምንድን ናቸው?የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
-
-
“ወደ አምላክ መንግሥት መግባት” ሲባል ምን ማለት ነው?
ቃል በቃል ‘ወደ አምላክ መንግሥት የሚገቡ’ ሰዎች ወደ ሰማይ በመሄድ ከኢየሱስ ጋር አብረው ይገዛሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ‘በዙፋን እንደሚቀመጡ’ እንዲሁም ‘በምድር ላይ ነገሥታት ሆነው እንደሚገዙ’ ይናገራል።—ሉቃስ 22:29, 30፤ ራእይ 5:9, 10
-