የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ደም ለሕይወት በጣም አስፈላጊ ነው
    ደም ሕይወትህን ሊያድን የሚችለው እንዴት ነው?
    • ኢየሱስ ከሞተ ከበርካታ ዓመታት በኋላ ክርስቲያን የሚሆን ሰው ለእስራኤላውያን የተሰጡትን ሕጎች በሙሉ መጠበቅ ይኖርበታል ወይስ አይኖርበትም የሚል ጥያቄ በተነሳ ጊዜ የሆነውን ነገር ልብ በል። በዚህ ጥያቄ ላይ ውይይት የተደረገው ሐዋርያት በአባልነት ይገኙበት በነበረው የክርስቲያኖች የአስተዳደር አካል ምክር ቤት ነበር። የኢየሱስ የእናቱ ልጅ የሆነው ያዕቆብ ለኖኅና ለእስራኤል ብሔር ስለ ደም የተሰጠው ሕግ ከሚገኝባቸው ጽሑፎች ጠቅሷል። ይህ ሕግ በክርስቲያኖች ላይ ተፈጻሚነት ይኖረዋልን?​​—⁠ሥራ 15:​1-21

      ይህ ምክር ቤት የደረሰበትን ውሳኔ ለጉባኤዎች በሙሉ አስተላለፈ። ክርስቲያኖች ለሙሴ የተሰጠውን ሕግ መጠበቅ አያስፈልጋቸውም። ነገር ግን “ለጣዖት ከተሠዋ፣ ከደምም፣ ከታነቀም [ደሙ ያልፈሰሰ ሥጋ] ከዝሙትም” ‘መራቅ እንደሚያስፈልጋቸው’ ገልጸዋል። (ሥራ 15:​22-29) ሐዋርያት የአመጋገብን ሥርዓት የሚመለከት ተራ ደንብ ማስተላለፋቸው አልነበረም። ውሳኔያቸው የጥንቶቹ ክርስቲያኖች በጥብቅ የተከተሉትን መሠረታዊ የሆነ የግብረ ገብ ደንብ የሚደነግግ ነበር። ይህ ከሆነ አሥር ዓመት ከሚያክል ጊዜ በኋላም “ለጣዖት ከተሠዋ፣ ከደምም፣ ከታነቀም፣ ከዝሙትም ነፍሳቸውን” መጠበቅ እንደሚያስፈልጋቸው ገልጸዋል።​—⁠ሥራ 21:​25

      በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች አዘውትረው ወደ ቤተ ክርስቲያን እንደሚሄዱ ታውቃለህ። ከነዚህ መካከል አብዛኞቹ የክርስትና ግብረ ገብ ጣዖት አለማምለክንና ዝሙት አለመፈጸምን እንደሚጨምር ይስማሙ ይሆናል። ይሁን እንጂ ሐዋርያት ደም መውሰድን ከእነዚህ ክፉ ድርጊቶች ጋር በእኩል ደረጃ እንዳስቀመጡ ልብ ማለት አስፈላጊ ነው። ውሳኔያቸውን ሲያጠቃልሉ እንዲህ ብለዋል:- “ከዚህም ሁሉ ራሳችሁን ብትጠብቁ በመልካም ትኖራላችሁ። ጤና ይስጣችሁ።”​—⁠ሥራ 15:​29

      ሐዋርያዊው ድንጋጌ በክርስቲያኖች ሁሉ ላይ ተፈጻሚነት እንዳለው ከጥንት ዘመን ጀምሮ ይታመን ነበር። ዩሴቢየስ በሁለተኛው መቶ ዘመን መጨረሻ ገደማ ላይ ትኖር የነበረች አንዲት ሴት ብዙ ሥቃይ ደርሶባት ልትሞት በተቃረበችበት ጊዜ ክርስቲያኖች “የማሰብ ችሎታ የሌላቸውን እንስሳት ደም እንኳን መብላት አልተፈቀደላቸውም” እንዳለች ጽፏል። ይህች ሴት የመሞት መብት ያላት መሆኑን ለማረጋገጥ ስትል የተናገረችው አልነበረም። በሕይወት የመኖር ፍላጎት የነበራት ቢሆንም ለመኖር ስትል የምታምንበትን መሠረታዊ ሥርዓት ለመጣስ አልፈለገችም። የሚያምኑበትን መሠረታዊ ሥርዓት ከግል ጥቅማቸው የሚያስቀድሙ ሰዎችን በአክብሮት አትመለከትምን?

      ጆሴፍ ፕርስትሊ የተባሉት የሳይንስ ሊቅ እንዲህ ብለዋል:- “ለኖህ የተሰጠው ደም መብላትን የሚከለክለው ሕግ በዘሮቹ ሁሉ ላይ የተጣለ ግዴታ ይመስላል። . . . የሐዋርያትን ድንጋጌ፣ የድንጋጌውን ባሕርይና ስፋት በትክክል አልተረዱም ሊባሉ የማይችሉት የጥንት ክርስቲያኖች በነበራቸው ምግባር መሠረት እንደምንረዳው ከሆነ ፍጹማዊና ዘላለማዊ ሕግ እንዲሆን የታቀደ ነበር ከሚለው መደምደሚያ ልናመልጥ አንችልም። ምክንያቱም ክርስቲያኖች ለበርካታ መቶ ዘመናት ደም አይበሉም ነበር።”

  • ደም ለሕይወት በጣም አስፈላጊ ነው
    ደም ሕይወትህን ሊያድን የሚችለው እንዴት ነው?
    • [በገጽ 4 ላይ የሚገኝ ሣጥን]

      “ቁርጥ ባለና በማያሻማ ቃል [በሥራ 15 ላይ] የተነገረው ደንብ ሊሻር የማይችል እንደሆነ ስለተገለጸ ሐአዋርያት ለጊዜው ብቻ የሚቆይ፣ ዘላቂ ያልሆነ ሕግ እንደሆነ አድርገው እንዳልተመለከቱት ጠንካራ ማስረጃ ይአሆናል።”​—⁠የስታስበርግ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ኤድዋርድ ሩስ

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ