-
በፍቅር እርስ በርስ ተስማምቶ መኖርበምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ
-
-
8. (ሀ) በጳውሎስና በበርናባስ መካከል ምን ችግር ተፈጠረ? (ለ) በቦታው ብትገኝና ችግሩን ብታይ ኖሮ ምናልባት ምን ብለህ ትደመድም ነበር?
8 አንድ ጊዜ በሐዋርያው ጳውሎስና የጉዞ ጓደኛው በነበረው በበርናባስ መሀከል ችግር ተነሥቶ ነበር። ለሁለተኛው ሚስዮናዊ ጉዞአቸው ሲነሡ በርናባስ የአጎቱን ልጅ ማርቆስን አብሮ ለመውሰድ ፈልጎ ነበር። ይሁን እንጂ ማርቆስ በመጀመሪያው ሚስዮናዊ ጉዞአቸው ወቅት ትቷቸው ወደ ቤቱ ተመልሶ ስለነበረ ጳውሎስ አሁን ማርቆስን ይዞ ለመሄድ አልፈለገም። (ሥራ 13:13) መጽሐፍ ቅዱስ “እርስ በርሳቸው እስኪለያዩ ድረስ መከፋፋት ሆነ” ይላል። (ሥራ 15:37-40) ይህ ይሆናል ብለህ ልታስበው ትችላለህን? አንተ በቦታው ተገኝተህ ቢሆንና የተፈጠረውን “መከፋፋት” ብታይ ኖሮ ሁለቱም ባሳዩት ጠባይ ምክንያት የአምላክ ድርጅት አባሎች አይደሉም ብለህ ትደመድም ነበርን?
-
-
በፍቅር እርስ በርስ ተስማምቶ መኖርበምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ
-
-
11. (ሀ) ጳውሎስና በርናባስ በቁጣ ቢገነፍሉም እውነተኛ ክርስቲያኖች መሆናቸውን ያሳዩት እንዴት ነው? (ለ) ከምሳሌያቸው እንዴት ልንጠቀም እንችላለን?
11 በጳውሎስና በበርናባስ መካከል ተነሥቶ የነበረው ችግርስ ምን ሆነ? ይኸኛውም ቢሆን በፍቅር መፍትሔ አግኝቷል ምክንያቱም በሌላ ጊዜ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ጉባኤ ደብዳቤ ሲጽፍ በርናባስ የቅርብ የሥራ ጓደኛው መሆኑን ተናግሯል። (1 ቆሮንቶስ 9:5, 6) ምንም እንኳ ጳውሎስ ማርቆስን የጉዞ ጓደኛው አድርጎ ለመምረጥ እንዲጠራጠር ያበቃው ጥሩ ምክንያት ቢኖረውም ይህ ወጣት ከጊዜ በኋላ ብስለት ስላገኘ ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ እንዲህ ብሎ ለመጻፍ ችሏል:- “ማርቆስ ለአገልግሎት ብዙ ይጠቅመኛልና ይዘኸው ከአንተ ጋር አምጣው።” (2 ጢሞቴዎስ 4:11) ችግሮችን እንዴት መፍታት እንደሚቻል ከሚያሳየው ከዚህ ምሳሌ ጥቅም ለማግኘት እንችላለን።
-